ሕዝቅኤል 16:33 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 አመንዝራ ሴት ገንዘብ ይከፈላት ነበር፤ አንቺ ግን ገንዘብ በመቀበል ፈንታ ለወዳጆችሽ ስጦታ ታበረክቺአለሽ፤ ከየአቅጣጫው መጥተው ከአንቺ ጋር ያመነዝሩ ዘንድ መደለያ ገንዘብ ሰጠሽ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም33 ማንኛዋም አመንዝራ ሴት ዋጋ ይከፈላታል፤ አንቺ ግን ለወዳጆችሽ ሁሉ ስጦታ ታበረክቻለሽ፤ ከየአቅጣጫው መጥተው ከአንቺ ጋራ ያመነዝሩ ዘንድ እጅ መንሻ ታቀርቢላቸዋለሽ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 ለአመንዝራዎች ሁሉ ሥጦታ ይሰጡአቸዋል፥ አንቺ ግን ለወዳጆችሽ ሁሉ ሥጦታሽን ትሰጫለሽ፥ ለአመንዝራነትሽ ከየአቅጣጫው ወደ አንቺ እንዲገቡ ጉቦ ትሰጫቸዋለሽ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 ለአመንዝራዎች ሁሉ ዋጋ ይሰጡአቸዋል፤ አንቺ ግን ለወዳጆችሽ ሁሉ ዋጋ ትሰጫለሽ፤ ከአንቺም ጋር ለማመንዘር በዙሪያሽ ይገቡብሽ ዘንድ መማለጃን ትሰጫቸዋለሽ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)33 ለጋለሞቶች ሁሉ ዋጋ ይሰጡአቸዋል፥ አንቺ ግን ለውሽሞችሽ ሁሉ ዋጋ ትሰጫለሽ፥ ከአንቺም ጋር ለማመንዘር በዙሪያሽ ይገቡብሽ ዘንድ መማለጃ ትሰጫቸዋለሽ። 参见章节 |