Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 16:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ልጆቼን በማረድ ለጣዖቶች መሥዋዕት አድርገሽ አቀረብሽ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ልጆቼን ዐርደሽ ለጣዖት መሥዋዕት አድርገሽ አቀረብሻቸው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ልጆቼን አረድሽ፥ በእነርሱም በኩል ስታልፊ ለእነርሱ ሰጠሻቸው፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ልጆ​ችን አረ​ድሽ፤ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትም አሳ​ል​ፈሽ ሰጠሽ፤ በውኑ ግል​ሙ​ት​ናሽ ጥቂት ነውን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ልጆቼን አረድሽ፥ ለእነርሱም በእሳት በኩል አሳልፈሽ ሰጠሽ፥ በውኑ ግልሙትናሽ ጥቂት ነውን?

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 16:21
11 交叉引用  

ለእነዚያም አሕዛብ አማልክት ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ፤ ከሙታን ጠሪዎችና ከጠንቋዮችም ምክር ጠየቁ፤ እግዚአብሔር ለሚጠላው ክፉ ነገር ሁሉ ራሳቸውን አሳልፈው በመስጠት የእግዚአብሔርን ቊጣ አነሣሡ።


የገዛ ልጁንም መሥዋዕት አድርጎ አቀረበ፤ እርሱም ራሱ ሟርተኛና አስማተኛ ሆኖ ከጠንቋዮችና ከሙታን ጠሪዎች ምክርን ይጠይቅ ነበር፤ በዚህም ሁሉ አድራጎቱ ታላቅ ኃጢአት በመሥራቱ የእግዚአብሔርን ቊጣ አነሣሣ።


ንጉሥ ኢዮስያስ በሒኖም ሸለቆ የነበረው “ቶፌት” ተብሎ የሚጠራው የአሕዛብ ማምለኪያ ቦታ የረከሰ መሆኑን አስገነዘበ፤ ከዚህም የተነሣ “ሞሌክ” ተብሎ ለሚጠራው አምላክ ወንድ ልጁን ወይም ሴት ልጁን መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርብ ማንም እንዳይኖር ተከለከለ፤


በሂኖም ሸለቆም ዕጣን አጠነ፤ እስራኤላውያን ወደ ምድሪቱ በገቡ ጊዜ እግዚአብሔር ከዚያ ያባረራቸውን ሕዝቦች አጸያፊ ልማድ በመከተል፥ የራሱን ወንዶች ልጆች እንኳ ሳይቀር የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ለጣዖቶች አቀረበ።


ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን ለአጋንንትና በከነዓን አገር ለሚገኙ ጣዖቶች መሥዋዕት አድርገው አቀረቡ።


“ከእስራኤል ሕዝብም ሆነ ከእንስሶቹ በኲር ሆኖ የተወለደ ሁሉ ለእኔ መሆን ይገባዋል፤ ስለዚህ በኲር ሆኖ የተወለደውን ሁሉ ለእኔ እንዲሆን ቀድሰው።”


ልጆቻቸውንም መሥዋዕት አድርገው በእሳት ለማቃጠል ለባዓል መሠዊያዎችን ሠርተዋል፤ ይህን እንዲያደርጉ አላዘዝኳቸውም፤ ከቶም ስለዚህ ነገር አላሰብኩም።


የበኲር ልጆቻቸውን እስከ መሠዋት ድረስ ተቀባይነት የሌለውን መሥዋዕት በማቅረብ ራሳቸውን እንዲያረክሱ ተውኳቸው፤ ይህንንም ያደረግኹት እነርሱን መቀጣጫ የማደርጋቸው እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቁ ዘንድ ነው።


የእግዚአብሔር አምላክህን ስም እንዳታሰድብ ከልጆችህ ማንኛውንም ሞሌክ ለተባለው ባዕድ አምላክ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆን ዘንድ አሳልፈህ አትስጥ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


ማንም ከመካከልህ ወንድ ልጁን፥ ወይም ሴት ልጁን በእሳት የሚሠዋ አይኑር፤ ወይም አስማተኛ፥ ሟርተኛ፥ ጠንቋይ፥ መተተኛ አይሁን።


跟着我们:

广告


广告