Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 16:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ምርጥ የሆነ ዱቄት የወይራ ዘይትና ማር. ምግብ እንዲሆንሽ ሰጥቼሽ ነበር፤ አንቺ ግን ጣዖቶችን ለማስደሰት መልካም መዓዛ ያለው መሥዋዕት አድርገሽ አቀረብሽ፤” ይህም ተደርጓል፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 እንድትበዪ የሰጠሁሽን ምግብ ይኸውም ምርጡን ዱቄት፣ ማሩንና የወይራ ዘይቱን መልካም መዐዛ ያለው ዕጣን አድርገሽ አቀረብሽላቸው፤ እንዲህ ያለ ነገር ተፈጽሟል፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 የሰጠሁሽን ምግቤን፥ እንድትበይው የሰጠሁሽን ምርጥ ዱቄት፥ ዘይትና ማር ጣፋጭ ሽታ አድርገሽ በፊታቸው አስቀመጥሽ፥ እንዲህም ተደርጓል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 የሰ​ጠ​ሁ​ሽ​ንም እን​ጀ​ራ​ዬን፥ ያበ​ላ​ሁ​ሽ​ንም ዱቄ​ትና ዘይ​ቱን፥ ማሩ​ንም ጣፋጭ ሽታ አድ​ር​ገሽ በፊ​ታ​ቸው አኖ​ርሽ፤ እን​ዲ​ህም ሆኖ​አል፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 የሰጠሁሽንም እንጀራዬን ያበላሁሽንም መልካሙን ዱቄትና ዘይቱን ማሩንም ጣፋጭ ሽታ አድርገሽ በፊታቸው አኖርሽ፥ እንዲሁም ሆኖአል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 16:19
7 交叉引用  

የመሥዋዕቱም መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ በሐሳቡም እንዲህ አለ፥ ገና ከሕፃንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ መሆኑን ስለማውቅ፤ “ሰው በሚፈጽመው በደል ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ በአሁኑ ጊዜ እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።


ነገር ግን አሳፋሪ ለሆኑ ጣዖቶች መስገዳችን፥ የበግና የከብት መንጋዎቻችንን ሁሉ፥ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንን ሁሉ፥ ከጥንት ጀምሮ የቀድሞ አባቶቻችን ደክመው ያፈሩልንን ሀብት ሁሉ እንድናጣ አድርጎናል።


ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ብዙ ጌጣጌጦች ነበሩሽ፤ ከልዩ ልዩ ሐር የተሠሩና በጥልፍ ጌጥ የተዋቡ ውድ ልብሶች ነበሩሽ፤ ምርጥ ከሆነ ዱቄት የተጋገረ ዳቦ፥ ማርና የወይራ ዘይት ትመገቢ ነበር፤ ውበትሽ እጅግ እየጨመረ ስለ ሄደ ንግሥት ለመሆን በቃሽ።


እኔ የሰጠሁሽንም በጥልፍ ያጌጡ ልብሶችሽንም ወስደሽ ምስሎቹን አለበስሽ፤ እኔ የሰጠሁሽንም የወይራ ዘይትና ዕጣን ለምስሎቹ አቀረብሽ።


መመኪያቸው ከሆኑት ውብ ጌጦቻቸው አስጠሊና አጸያፊ ጣዖቶቻቸውን ሠሩባቸው፤ ስለዚህ እነዚህን ጌጦቻቸውን በእነርሱ ዘንድ አረክሳቸዋለሁ።


跟着我们:

广告


广告