Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 16:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እኔ የሰጠሁሽን ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ጌጣጌጦችን ወስደሽ የወንድ ጣዖቶችን በመሥራት ከእነርሱ ጋር አመነዘርሽ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ከሰጠሁሽ ወርቄና ብሬ የተሠራውን ምርጥ ጌጣጌጥ ወስደሽ የወንድ ምስሎች ለራስሽ አበጀሽ፤ ከእነርሱም ጋራ ዝሙት ፈጸምሽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 የሰጠሁሽን ከወርቄና ከብሬ የተሠራውን የሚያምር ጌጣጌጥ ወስደሽ የወንድ ምስሎች ለራስሽ ሠራሽ፥ ከእነርሱም ጋር አመነዘርሽ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ከሰ​ጠ​ሁ​ሽም ከወ​ር​ቄና ከብሬ የተ​ሠ​ራ​ውን የክ​ብ​ር​ሽን ዕቃ ወስ​ደሽ የወ​ንድ ምስ​ሎ​ችን ለራ​ስሽ አድ​ር​ገ​ሻል፤ አመ​ን​ዝ​ረ​ሽ​ባ​ቸ​ው​ማል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ከሰጠሁሽም ከወርቄና ከብሬ የተሠራውን የክብርሽን ዕቃ ወስደሽ የወንድ ምስሎች ለራስሽ አድርገሻል አመንዝረሽባቸውማል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 16:17
14 交叉引用  

ከቶም አላፈረችም፤ ይልቁንም ድንጋይና ዛፍ በማምለክ ምድሪቱን አረከሰች።


በጌጥ አስጌጥኩሽ፤ የእጅ አንባርና የአንገት ድሪ አደረግሁልሽ።


ለአፍንጫሽ ቀለበት፥ ለጆሮሽ ጒትቻ፥ እንዲሁም በራስሽ ላይ የምትደፊው ውብ የሆነ አክሊል ሰጠሁሽ።


ከብርና ከወርቅ የተሠሩ ብዙ ጌጣጌጦች ነበሩሽ፤ ከልዩ ልዩ ሐር የተሠሩና በጥልፍ ጌጥ የተዋቡ ውድ ልብሶች ነበሩሽ፤ ምርጥ ከሆነ ዱቄት የተጋገረ ዳቦ፥ ማርና የወይራ ዘይት ትመገቢ ነበር፤ ውበትሽ እጅግ እየጨመረ ስለ ሄደ ንግሥት ለመሆን በቃሽ።


ከልብሶችሽ ጥቂቱን ወስደሽ የመስገጃ ስፍራዎችሽን አስጌጥሽባቸው፤ በዚያም አመንዝራነትሽን ቀጠልሽ፤ እነዚህ ድርጊቶች መፈጸም አልነበረባቸውም፤ ከቶም መፈጸም አይገባቸውም፤


እኔ የሰጠሁሽንም በጥልፍ ያጌጡ ልብሶችሽንም ወስደሽ ምስሎቹን አለበስሽ፤ እኔ የሰጠሁሽንም የወይራ ዘይትና ዕጣን ለምስሎቹ አቀረብሽ።


የእስራኤል ሕዝብ ብዙ ዘለላ እንደ ያዘ የወይን ተክል ናቸው፤ ፍሬ በበዛላቸው መጠን ብዙ የጣዖት መሠዊያዎችን ሠሩ፤ ምድራቸው ፍሬያማ ሆና በበለጸገችላቸው መጠን የጣዖት መስገጃ ዐምዶችን አስጊጠው ሠሩ።


“በዓል” ለሚባለው ጣዖት ለማጠንና ጌጣጌጥዋን አድርጋ ፍቅረኛዎችዋን በመከተል እኔን በመተዋ እቀጣታለሁ፤ ይላል እግዚአብሔር።


跟着我们:

广告


广告