ሕዝቅኤል 16:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ከልብሶችሽ ጥቂቱን ወስደሽ የመስገጃ ስፍራዎችሽን አስጌጥሽባቸው፤ በዚያም አመንዝራነትሽን ቀጠልሽ፤ እነዚህ ድርጊቶች መፈጸም አልነበረባቸውም፤ ከቶም መፈጸም አይገባቸውም፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ከልብስሽ አንዳንዱን ወስደሽ የምታመነዝሪበትን መስገጃ ስፍራ አስጌጥሽበት፤ እንዲህ ዐይነት ነገር ከዚህ ቀደም አልታየም፤ ወደ ፊትም አይኖርም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ከልብሶችሽ ጥቂቱን ወስደሽ የመስገጃ ስፍራዎችሽ ላይ በዝንጉርጉር ልብስ ያስጌጥሻቸውን መስገጆች ለራስሽ ሠራሽ በዚያም ገለሞትሽ፥ እንዲህም ያለ ነገር ከአሁን በፊት አልነበረም፥ ከእንግዲህም ወዲያ አይሆንም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ከልብስሽም ወስደሽ በመርፌ የተጠለፉ ጣዖታትን ሠራሽ፤ አመነዘርሽባቸውም፤ ስለዚህ ፈጽመሽ አልገባሽም፤ ከእንግዲህም ወዲህ እንዲህ ያለ ነገር አይሆንም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ከልብስሽም ወስደሽ በኮረብቶች ላይ በዝንጕርጕር ልብስ ያስጌጥሻቸውን መስገጆች ለራስሽ ሠራሽ በዚያም ገለሞትሽ፥ እንዲህም ያለ ነገር ከአሁን በፊት አልነበረም፥ ከእንግዲህም ወዲያ አይሆንም። 参见章节 |