Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 15:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የእሳት ማቀጣጠያ ከመሆን በቀር ሌላ ጥቅም የለውም፤ ጫፎቹ ነደው መካከሉ ካረረ በኋላ በእርሱ አንድ ነገር እንኳ መሥራት ይቻላልን?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እንዲነድድ እሳት ላይ ከተጣለ በኋላ፣ እሳቱ ጫፍና ጫፉን አቃጥሎ፣ መኻሉን ከለበለበው፣ ለአንዳች ነገር ይጠቅማልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እነሆ ለመቃጠል ለእሳት ተስጥቷል፥ እሳቱም ሁለቱን ጫፎቹን በልቶታል፥ መካከሉም ተቃጥሏል፥ ለሥራ ይጠቅማልን?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እነሆ ለመ​ቃ​ጠል በእ​ሳት ላይ ተጥ​ሎ​አል፤ እሳ​ቱም ሁለ​ቱን ጫፎ​ቹን በል​ቶ​አል፤ መካ​ከ​ሉም ተቃ​ጥ​ሎ​አል፤ በውኑ ለሥራ ይጠ​ቅ​ማ​ልን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እነሆ፥ ለመቃጠል በእሳት ላይ ተጥሎአል፥ እሳቱም ሁለቱን ጫፎቹን በልቶአል፥ መካከሉም ተቃጥሎአል፥ በውኑ ለሥራ ይጠቅማልን?

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 15:4
13 交叉引用  

ጠላቶች ቈራርጠው በእሳት አቃጥለዋታል፤ በቊጣህ ተመልከታቸው፤ አጥፋቸውም!


ገለባ በእሳት ብልጭታ እንደሚጋይ “ኀይለኞች ነን” የሚሉ ሰዎች ይጠፋሉ፤ እንደ ቃጠሎ እሳት በእነርሱ ላይ የሚመጣውን ጥፋት የሚያቆም የለም።


የዛፍ ቅርንጫፎች በሚደርቁበትም ጊዜ ይሰባበራሉ፤ ሴቶችም ለእሳት ማገዶ ይለቅሙአቸዋል፤ ሕዝቡ ማስተዋል ስለ ጐደለው ፈጣሪ አምላኩ አይራራለትም፤ ምንም ምሕረት አያደርግለትም።


አንድ ነገር እንኳ ለመሥራት ይጠቅማልን? የዕቃ መስቀያ ኩላብ እንኳ ከእርሱ ሊሠራ ይችላልን?


ከመቃጠሉ በፊት እንኳ ዋጋቢስ ከነበረ አሁንማ እሳቱ ካቃጠለውና ካሳረረው በኋላ የባሰውን ጥቅም የሌለው ይሆናል።”


ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በዱር ካሉ ዛፎች መካከል የወይንን ግንድ ለማገዶ እንዳደረግሁት የኢየሩሳሌምን ሕዝብ እንዲሁ አደርገዋለሁ።


ከወይን ተክሉ ግንድ እሳት ወጣ፤ ቅርንጫፎቹንና ፍሬውን ሁሉ እሳት በላው፤ ቅርንጫፎቹ ዳግመኛ ብርቱ አይሆኑምና በትረ መንግሥት መሆንም አይችሉም። እንግዲህ በመደጋገም የሚደረደረው ሙሾ ይህ ነው። እርሱም ለለቅሶ ያገለግላል።


“ሰዶምንና ገሞራን እንደ ደመሰስኩ ከእናንተም ብዙዎችን ደመሰስኩ፤ እናንተም የተረፋችሁት በእሳት ከተቀጣጠለ በኋላ ተነጥቆ እንደ ወጣ እንጨት ነው፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ወደ እኔ አልተመለሳችሁም።


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ ትዕቢተኞችና ክፉ አድራጊዎች እንደ ገለባ በእሳት የሚቃጠሉበት ጊዜ እየመጣ ነው፤ የሚመጣውም ከእነርሱ ሥር፥ ወይም ቅርንጫፍ ሳያስቀር ሁሉንም ያቃጥላል።


እርሱ መንሹ በእጁ ነው። በእርሱም አውድማውን ደኅና አድርጎ ያጠራል። ስንዴውን በጐተራ ይከተዋል፤ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


በእኔ የማይኖር እንደ ቅርንጫፍ ወደ ውጪ ተጥሎ ይደርቃል፤ እንዲህ ያሉት ቅርንጫፎች ተሰብስበው ወደ እሳት ይጣሉና ይቃጠላሉ።


አምላካችን እንደሚያቃጥል እሳት ነው።


እሾኽና አሜከላ ብታበቅል ግን ዋጋቢስ ትሆናለች፤ በቅርብ ጊዜም ትረገማለች፤ መጨረሻዋም በእሳት መቃጠል ነው።


跟着我们:

广告


广告