Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 14:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22-23 ሆኖም በኢየሩሳሌም ውስጥ ከእርስዋ ወደ እናንተ የሚመጡ ቅሬታዎች ይቀሩላታል፤ አካሄዳቸውንና ተግባራቸውን በምታዩበት ጊዜ የእነርሱን ሁኔታ ትረዳላችሁ፤ እናንተም በእነርሱ ላይ ያደረስኩት መቅሠፍት ሁሉ ያለምክንያት እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።” ይላል ልዑል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ነገር ግን ከዚያ ወጥተው የሚተርፉ ወንዶችና ሴቶች ልጆች አሉ፤ እነርሱም ወደ እናንተ ይመጣሉ፤ እናንተም አካሄዳቸውንና ተግባራቸውን በምታዩበት ጊዜ፣ በኢየሩሳሌም ላይ ስላመጣሁት መከራ፣ ስላደረስሁባትም አስከፊ ነገር ሁሉ ትጽናናላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ነገር ግን እነሆ፥ የሚያመልጡና ወንዶችንና ሴቶች ልጆችን የሚያወጡ ይቀሩላታል፥ እነሆ ወደ እናንተ ይመጣሉ፥ እናንተም መንገዳቸውንና ሥራቸውን ታያላችሁ፥ በኢየሩሳሌም ላይ ስላመጣሁት ክፉ ነገር፥ ስላመጣሁባትም ነገር ሁሉ ትጽናናላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ነገር ግን እነሆ የሚ​ያ​መ​ል​ጡና ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ችን ከእ​ር​ስዋ የሚ​ያ​ወጡ ይቀ​ሩ​ላ​ታል፤ እነሆ ወደ እና​ንተ ይወ​ጣሉ፤ እና​ን​ተም መን​ገ​ዳ​ቸ​ው​ንና ሥራ​ቸ​ውን ታያ​ላ​ችሁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ላይ ስላ​መ​ጣ​ሁት ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስላ​መ​ጣ​ሁ​ባ​ትም ነገር ሁሉ ትጽ​ና​ና​ላ​ችሁ፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ነገር ግን፥ እነሆ፥ የሚያመልጡና ወንዶችና ሴቶች ልጆችን የሚያመጡ ይቀሩላታል፥ እነሆ፥ ወደ እናንተ ይወጣሉ እናንተም መንገዳቸውንና ሥራቸውን ታያላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም ላይ ስላመጣሁት ክፉ ነገር ሁሉ ስላመጣሁባትም ነገር ሁሉ ትጽናናላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 14:22
27 交叉引用  

በሰይፍ ከመገደል የተረፉትንም ሁሉ ማርኮ ወደ ባቢሎን ወሰዳቸው፤ እነርሱም የፋርስ ንጉሠ ነገሥት መንግሥት እስከ ተነሣበት ጊዜ ድረስ፥ በዚያው በባቢሎን ባሪያዎች ሆነው፥ ንጉሥ ናቡከደነፆርንና የእርሱን ዘሮች ያገለግሉ ነበር።


በዓለም መንግሥታት ሁሉ ላይ የሚደርሰው ሁኔታ ይህ ነው፤ የወይራ ፍሬ ከዛፍ ሁሉ ላይ ተለቅሞ፥ የወይንም ዘለላ ከተሰበሰበ በኋላ እንደሚታይ የመከር መጨረሻ ይሆናል።


ከዐሥሩ አንድ ክፍል ቢተርፍም እንኳ እርሱም እንደ ግራር ወይም እንደ ዋርካ እንደገና ይቃጠላል። ዛፉ ሲቈረጥ ጉቶው ይቀራል። ጉቶውም የተቀደሰ ዘር ነው።”


እኔ ራሴ ከእናንተ ጋር በመሆን አድናችኋለሁ፤ እናንተን የበተንኩባቸውን አሕዛብ ሁሉ እደመስሳለሁ፤ እናንተን ግን አላጠፋም፤ ሆኖም ያለ ቅጣት አልተዋችሁም፤ የምቀጣችሁ ግን እንደ ጥፋታችሁ ነው፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


እነሆ እግዚአብሔር፥ ምድሪቱ ወደ ምድረ በዳነት እንደምትለወጥ፥ እስከ መጨረሻው ግን እንደማይደምስሳት ተነግሮአል።


ኤርምያስ ሆይ! ሕዝቡ ‘እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ነገር ያደረሰብን ስለምድን ነው?’ ብለው በጠየቁህ ጊዜ ከእኔ ተለይተው በገዛ ምድራቸው ላይ ባዕዳን አማልክትን እንዳመለኩ ሁሉ፥ እነርሱም ራሳቸው የእነርሱ ባልሆነ አገር የባዕድ ሕዝብ አገልጋዮች መሆናቸው እንደማይቀር ንገራቸው።”


ነገር ግን ከእነርሱ ጥቂቶቹን ከጦርነት፥ ከራብና ከቸነፈር እንዲተርፉ አደርጋለሁ፤ በዚህም ዐይነት በሕዝቦች መካከል ሲኖሩ ሥራቸው ምን ያኽል አጸያፊ እንደ ነበር ይገነዘባሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንኩ ያውቃሉ።”


አንቺም ውርደትሽን ተከናንበሽ ባደረግሽው ነገር ሁሉ ታፍሪአለሽ። ሰዶምና ሰማርያ ይህን ሁናቴሽን በሚያዩበት ጊዜ ያንቺን ያኽል ኃጢአተኞች ባለመሆናቸው ይጽናናሉ።


ይህንንም የማደርገው፥ ለፈጸምሽው በደል ሁሉ ይቅርታ ሳደርግልሽ ሥራሽን በማስታወስ በድንጋጤ ዐፍረሽ ጸጥ እንድትዪ ነው፤” ይህን የተናገረ ልዑል እግዚአብሔር ነው።


የፈጸማችኋቸውን አሳፋሪ ነገሮችና ራሳችሁንም እንዴት እንዳረከሳችሁ በዚያ ቦታ ታስታውሳላችሁ፤ በሠራችሁትም ክፉ ነገር ሁሉ ራሳችሁን እስከ መጸየፍ ትደርሳላችሁ።


እኔ ያን ዛፍ ወደ ሙታን ዓለም እንዲወርድ በማደርግበት ጊዜ አወዳደቁ የሚያሰማው ድምፅ ሕዝቦችን ሁሉ ያንቀጠቅጣል፤ ወደ ሙታን ዓለም የወረዱ የዔደን ዛፎችና የጥሩ መስኖ ውሃ የሚጠጡ የተመረጡ የሊባኖስ ዛፎች ሁሉ እርሱ ወደ ሙታን ዓለም በመውረዱ ደስ ይላቸዋል፤


“በሰይፍ የተገደሉት የግብጽ ንጉሥና ሠራዊቱ እነዚያን በሚያዩበት ጊዜ ወደ ሙታን ዓለም ስለ ወረዱት ብዛት ስላላቸው የግብጽ ሕዝብ ንጉሡ ይጽናናል፤ ይላል ልዑል እግዚአብሔር።


እነዚህ የእግዚአብሔር ሕዝብ ቢሆኑም እንኳ እርሱ ከሰጣቸው ምድር ወጥተዋል” ብለው የተበታተኑባቸው አገሮች ሕዝቦች ስለሚናገሩ ሕዝቤ ቅዱስ ስሜን አሰድበዋል።


መጥፎ ጠባያችሁንና ትፈጽሙት የነበረውንም ክፉ ሥራ ሁሉ ታስታውሳላችሁ፤ በኃጢአታችሁና ትፈጽሙት በነበረው የረከሰ ሥራ ምክንያት ራሳችሁን ትጸየፋላችሁ።


የሸለቆ ርግቦች ራሳቸውን ለማዳን ወደ ተራራ እንደሚወጡ እንዲሁም ከሰዎቹ መካከል ከሞት የተረፉ ካሉ በተራራ ላይ ተገኝተው በኃጢአታቸው ምክንያት እንደ ሸለቆ ርግቦች የሐዘን እንጒርጒሮ ያሰማሉ።


ከሞት የተረፉትም የእስራኤል ሕዝብ በብዙ ሕዝቦች መካከል እግዚአብሔር እንደሚልከው ጠልና በሣር እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ፤ ተማምነው የሚጠባበቁት ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ብቻ ይሆናል።


ጌታ እነዚያን ቀኖች ባያሳጥርማ ኖሮ ማንም መዳን ባልቻለም ነበር፤ ነገር ግን ለተመረጡት ሰዎች ሲባል እነዚያ ቀኖች ያጥራሉ።


እርሱም ይቅር ባይ አምላክ ስለ ሆነ አይተዋችሁም፤ ፈጽሞ እንድትደመሰሱም አያደርግም፤ ከቀድሞ አባቶቻችሁ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ከቶ አይረሳም።


跟着我们:

广告


广告