ሕዝቅኤል 14:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም21 ልዑል እግዚአብሔር የሚለው ይህ ነው፦ “ሕዝብንና እንስሶችን በአንድነት ለመጨረስ ጦርነትን፥ ራብን፥ አራዊትንና ቸነፈርን እነዚህን እጅግ የከፉ አራት መቅሠፍቶች በኢየሩሳሌም ላይ አመጣለሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም21 “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ ‘ሰውንና እንስሳቱን ለማጥፋት አራቱን አስፈሪ ፍርዶቼን፦ ሰይፍን፣ ራብን፣ የዱር አራዊትንና ቸነፈርን በኢየሩሳሌም ላይ በማመጣበት ጊዜ ምንኛ የከፋ ይሆን! 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)21 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ ፍርዶቼን ሰይፍ፥ ራብ፥ ክፉ አውሬና ቸነፈር፥ ሰውንና እንስሳን ከእርሷ ለማጥፋት ብሰድድም፥ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፥ “ይልቁንስ ሰውንና እንስሳን ከእርስዋ አጠፋ ዘንድ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ መቅሠፍቶችን፥ ሰይፍንና ራብን፥ ክፉዎችንም አውሬዎች፥ ቸነፈርንም ስሰድድባት፥ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)21 ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ይልቁንስ ሰውንና እንስሳን ከእርስዋ አጠፋ ዘንድ በኢየሩሳሌም ላይ አራቱን ክፉ ፍርዶቼን፥ ሰይፍንና ራብን ክፉዎችንም አውሬዎች ቸነፈርንም፥ ስሰድድባት! 参见章节 |