Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 13:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላቸዋል፦ “ሐሰትን ስለ ተናገራችሁና ራእያችሁም ውሸት ስለ ሆነ እኔ በእናንተ ላይ እነሣለሁ። ይህንን የተናገርኩ እኔ ጌታ እግዚአብሔር ነኝ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 “ ‘ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ቃላችሁ ሐሰት፣ ራእያችሁም ውሸት ስለ ሆነ እኔ በእናንተ ላይ ተነሥቻለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከንቱ ነገርን ስለ ተናገራችሁ፥ ውሸተኛ ራእይንም ስላያችሁ፥ እነሆ እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ከንቱ ነገ​ርን ስለ ተና​ገ​ራ​ችሁ፥ ሐሰ​ተኛ ራእ​ይ​ንም ስለ አያ​ችሁ፥ ስለ​ዚህ እነሆ እኔ በእ​ና​ንተ ላይ ነኝ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከንቱ ነገርን ስለ ተናገራችሁ ውሸተኛ ራእይንም ስላያችሁ፥ ስለዚህ፥ እነሆ፥ እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 13:8
21 交叉引用  

ከዚህ በኋላ ከቤትኤል የመጣው ሽማግሌ ነቢይ “እኔም እንዳንተው ነቢይ ነኝ፤ ከእኔ ጋር ወደ ቤቴ ወስጄ እንዳስተናግድህ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ነግሮኛል” አለው፤ ሽማግሌው ነቢይ የተናገረው ግን በመዋሸት ነበር።


አንቺም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ በሜዳ ላይ እንደሚገኝ ቋጥኝ ከሸለቆዎች በላይ ከፍ ብለሽ ትታዪአለሽ፤ ነገር ግን እኔ እዋጋሻለሁ፤ አንቺ ግን ማንም የሚደፍርሽና ምሽጎችሽን ጥሶ የሚገባ ያለ አይመስልሽም፤


አንዱ ከሌላው ቃልን በመስረቅ ‘ይህ የእግዚአብሔር ቃል ነው’ እያሉ የሚናገሩትን ነቢያት እጠላለሁ።


“እነሆ ተሰደው በባቢሎን ወደሚኖሩት ሁሉ ስለ ሽማዕያ የተነገረውን ይህን የትንቢት ቃል እንዲህ ብለህ ላክ፥ ‘ሽማዕያ እኔ ሳልከው የትንቢት ቃል በመናገር በውሸት እንድታምኑ አድርጓችኋል፤


ባቢሎን ሆይ! ምድርን በመላ የምታጠፊ አንቺ አጥፊ ተራራ ሆይ፥ እኔ ተቃዋሚሽ ነኝ፤ በአንቺ ላይ እጄን ዘርግቼ ከገደሉ ጫፍ ላይ አንከባልልሻለሁ፤ እንደ ተቃጠለ ተራራም አደርግሻለሁ።


እንዲህም በላት! ‘እኔ በአንቺ ላይ ተነሥቼአለሁ፤ ሰይፉን ከሰገባው አውጥቼ ኃጢአተኛውንና ጻድቁን ከመካከልሽ አጠፋለሁ።


“ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ጢሮስ ሆይ! እኔ በአንቺ ላይ ተነሥቼ ባሕር ሞገድን እንደሚያስነሣ በአንቺ ላይ ብዙ ሕዝቦቼን አስነሣለሁ።


ለሕዝብዋም ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል በላቸው፦ እኔ በእናንተ ላይ ተነሥቼአለሁ፤ በእናንተ ላይ በማደርገው ድርጊት ሕዝቦች ያመሰግኑኛል፤ ፍርዴን ተግባራዊ በማደርግበትና ቅድስናዬን በምገልጥበት ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ያውቃሉ።


እኔ በአንተና በወንዝህ ላይ በቊጣ ተነሥቻለሁ፤ በሰሜን ከሚግዶል ከተማ አንሥቼ በደቡብ እስከ አስዋን ከተማ ድረስ፥ እንዲያውም እስከ ኢትዮጵያ ጠረፍ ድረስ ግብጽን በሙሉ ምድረ በዳ አድርጌ ባዶዋን አስቀራታለሁ።


እኔ ልዑል እግዚአብሔር የበጎቹን እረኞች እቃወማለሁ፤ በጎቹን ከእረኞች እጅ ወስጄ እንዳያሰማሩአቸው አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ እረኞቹ ራሳቸውን አይመግቡም፤ ለእነርሱም ምግብ እንዳይሆኑ በጎቼን ከእነርሱ አፍ አስጥላለሁ።


እኔ ልዑል እግዚአብሔር የምለውንም ሁሉ እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘የኤዶም ሕዝብ ሆይ! እነሆ እኔ እናንተን እቃወማለሁ፤ ምድራችሁንም ባድማና ወና ላደርግ በእናንተ ላይ ተነሥቼአለሁ።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የሜሼክና የቱባል ሕዝብ ገዢ በሆነው በጎግ ላይ ትንቢት ተናገርበት፤ በእርሱም ላይ የተነሣሁ መሆኔን ንገረው።


በዚህም ምክንያት እኔ ልዑል እግዚአብሔር በአንቺ በኢየሩሳሌም ላይ በቊጣ የተነሣሁብሽ መሆኔን እገልጥልሻለሁ፤ ሕዝቦች ሁሉ እያዩ በፍርድ እቀጣሻለሁ።


ነነዌ ሆይ! በአንቺ ላይ ተነሥቼአለሁ ይላል የሠራዊት አምላክ፤ ሠረገሎችሽንም አቃጥላለሁ፤ ደቦሎችሽንም ሰይፍ ይበላቸዋል፤ በምድር ላይ በአንቺ ተጠቂ የሚሆን እንዳይኖር አደርጋለሁ፤ የመልእክተኞችሽም ድምፅ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።


መንፈስ ቅዱስ ግን በግልጥ እንዲህ ይላል፤ “በኋለኛው ዘመን አንዳንድ ሰዎች አሳሳች መናፍስትንና የአጋንንትን ትምህርት በመከተል ሃይማኖትን ይክዳሉ።”


በሰውነት ማጠንከሪያ ትምህርት ራስን ማለማመድ ጥቅሙ ጥቂት ነው፤ እግዚአብሔርን ማምለክ ማለማመድ ግን ለአሁንና ለሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለሁሉ ነገር ይጠቅማል።


የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ይመለከታሉ፤ ጆሮዎቹም ጸሎታቸውን ለመስማት ተከፍተዋል፤ በክፉ አድራጊዎች ላይ ግን ጌታ የቊጣ ፊቱን ያሳያል።”


跟着我们:

广告


广告