Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 12:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 የምትሄድበትን ስፍራ እንዳታይ ዕቃህን በትከሻህ ተሸክመህ ፊትህን በመሸፈን በጨለማ ስትሄድ ይመልከቱህ፤ እኔም ለእስራኤላውያን ምልክት አድርጌሃለሁ።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በፊታቸው ጓዝህን በትከሻህ ላይ አስቀምጥ፣ በምሽትም ተሸክመህ ውጣ። ለእስራኤል ቤት ምልክት አድርጌሃለሁና ምድሪቱን እንዳታይ ፊትህን ሸፍን።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ለእስራኤልም ቤት ምልክት አድርጌሃለሁና እያዩህ በትከሻህ ላይ ተሸከመው፥ በጨለማም ይዘኸው ውጣ፥ ምድሪቱንም እንዳታይ ፊትህን ሸፍን።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ምል​ክት አድ​ር​ጌ​ሃ​ለ​ሁና በፊ​ታ​ቸው ዕቃ​ህን በት​ከ​ሻህ ላይ አን​ግ​ተው፤ በጨ​ለ​ማም ተሸ​ክ​መህ ውጣ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም እን​ዳ​ታይ ፊት​ህን ሸፍን።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ለእስራኤልም ቤት ምልክት አድርጌሃለሁና በፊታቸው በጫንቃህ ላይ አንግተው፥ በጨለማም ተሸክመህ ውጣ፥ ምድሪቱንም እንዳታይ ፊትህን ሸፍን።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 12:6
12 交叉引用  

ዳዊትም ሐዘኑን በመግለጥ ጫማ ሳያደርግ ራሱን ተከናንቦ የደብረ ዘይትን አቀበት እያለቀሰ ወጣ፤ የተከተሉትም ሁሉ ደግሞ ራሳቸውን ተከናንበው ያለቅሱ ነበር።


ከዚህም በኋላ ቀኑ ሊመሽ ሲል ወደ ሶርያውያን ሰፈር ሄዱ፤ ነገር ግን እዚያ ሲደርሱ ማንም ሰው አልነበረም፤


የጨለማ ሽብር ስለሚያስደስታቸው ለሁሉም ድቅድቅ ጨለማ ማለዳቸው ነው።”


እነሆ፥ ልጆቼና እኔ በጽዮን ተራራ ላይ ከሚኖረው ከሠራዊት አምላክ ለእስራኤል ሕዝብ የተሰጠን የማስጠንቀቂያ ምልክት ነን።


ነገር ግን እኔ መረቤን ዘርግቼ አጠምደዋለሁ፤ በዐይኑ ሳያያት ወደሚሞትባት ወደ ባቢሎን ከተማ አመጣዋለሁ፤


በሚመለከቱህም ጊዜ የቤትህን ግድግዳ ሸንቁረህ ቀዳዳ አብጅ፤ ዕቃህንም በዚያ ቀዳዳ አሾልከህ አውጣው፤


በዚህም ዐይነት ሕዝቅኤል ለእናንተ ምልክት ይሆናል፤ እርሱ እንዳደረገውም ታደርጋላችሁ፤’ ይህ በሚፈጸምበት ጊዜ እኔ ልዑል እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


የብረት ምጣድም ወስደህ በአንተና በከተማይቱ መካከል እንደ ቅጽር አቁመው፤ ፊትህንም ወደ ከተማይቱ አቅና፤ የተከበበችም ትምሰል፤ የምትከባትም አንተው ነህ፤ ይህም ለእስራኤል ሕዝብ ምልክት ይሆናል።


ሊቀ ካህናት ኢያሱ ሆይ! ይህን ስማ፤ እናንተም ከእርሱ ጋር በክህነት የምታገለግሉና ወደ ፊት ለሚሆነው መልካም ነገር ምልክት የምትሆኑ ይህን አድምጡ፤ ‘ቅርንጫፍ’ ተብሎ የሚጠራውን አገልጋዬን ወደ ፊት እልካለሁ።


ሳኦልም ልብሱን ለውጦ ማንነቱ እንዳይታወቅ በማድረግ በሌሊት ሁለት ሰዎች አስከትሎ ሴትዮዋን ለማየት ሄደ፤ እዚያም እንደ ደረሰ “መናፍስትን ጠይቀሽ ወደ ፊት ስለሚሆነው ነገር አስረጂኝ፤ ስሙንም የምጠራልሽን ሰው አስነሽልኝ” አላት።


跟着我们:

广告


广告