Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 12:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ነገር ግን እኔ መረቤን ዘርግቼ አጠምደዋለሁ፤ በዐይኑ ሳያያት ወደሚሞትባት ወደ ባቢሎን ከተማ አመጣዋለሁ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 መረቤን በርሱ ላይ እዘረጋለሁ፤ በወጥመዴም ይያዛል፤ ወደ ከለዳውያን ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፤ ነገር ግን እርሷን ሳያያት በዚያ ይሞታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፥ በወጥመዴም ይያዛል፥ ወደ ከለዳውያን ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፥ ሆኖም አያያትም በዚያም ይሞታል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 መረ​ቤ​ንም በእ​ርሱ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለሁ፤ በወ​ጥ​መ​ዴም ይያ​ዛል፤ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር ወደ ባቢ​ሎን አመ​ጣ​ዋ​ለሁ፤ ሆኖም አያ​ያ​ትም፤ በዚ​ያም ይሞ​ታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ በወጥመዴም ይያዛል፥ ወደ ከለዳውያንም ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፥ ሆኖም አያያትም በዚያም ይሞታል።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 12:13
24 交叉引用  

በመሬት ላይ የሸምቀቆ ገመድ ተዘርግቶለታል፤ በመንገዱም ወጥመድ ተዘጋጅቶአል።


ነገር ግን ይህን ሁሉ መከራ ያደረሰብኝና መረብ ውስጥም የጣለኝ እግዚአብሔር መሆኑን እንድታውቁ እወዳለሁ።


በክፉዎች ላይ የእሳት ፍምንና ዲንን ያዘንባል፤ የሚጋረፍ ነፋስም የእነርሱ ዕድል ፈንታ ነው።


በወጥመድ አጠመድከን፤ ከባድ ሸክምንም ጫንክብን።


“የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስንና በዙሪያው ያሉትን አማካሪዎቹን፥ እንዲሁም ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በዚህች ምድር የተረፉትንና ወደ ግብጽ የወረዱትን ሁሉ ግን ለምግብነት ደስ እንደማያሰኙና እጅግ እንደተበላሹት እንደእነዚያ የበለስ ፍሬዎች አደርጋቸዋለሁ።


ሴዴቅያስ ወደ ባቢሎን ይወሰዳል፤ እኔ በሞት እስክጐበኘው ድረስ በዚያ ይኖራል፤ ከባቢሎናውያን ጋር ለመዋጋት ቢሞክር እንኳ አይሳካለትም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


አንተም ማምለጥ አትችልም፤ ትማረካለህ፤ ለእርሱም ተላልፈህ ትሰጣለህ፤ እርሱን በቀጥታ ፊት ለፊት ታየዋለህ፤ እርሱም ያነጋግርሃል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ባቢሎን ትሄዳለህ፤


ዘግየት ብሎም ንጉሥ ሴዴቅያስ መልእክተኛ ልኮ አስወሰደኝና በቤተ መንግሥቱ በግል ሲያነጋግረኝ “ከእግዚአብሔር የተነገረህ የትንቢት ቃል አለን?” ብሎ ጠየቀኝ። “አዎ፥ አለ!” ብዬ ንግግሬን በመቀጠል “አንተ ለባቢሎን ንጉሥ ተላልፈህ ትሰጣለህ” አልኩት።


ከዚህም ሁሉ በኋላ የሴዴቅያስን ዐይኖች አወጣ፤ ወደ ባቢሎንም ለመውሰድ በነሐስ ሰንሰለት አሰረው።


ባቢሎን ሆይ! በራስሽ ላይ ባጠመድሽው ወጥመድ ሳታውቂው ተያዝሽበት፤ ተይዘሽ የተጋለጥሽውም እግዚአብሔርን ስለ ተዳፈርሽ ነው።


“ከላይ እሳት ላከ፤ እሳቱም ወደ አጥንታችን ዘለቀ፤ ለእግራችን መረብ ዘረጋ፤ ወደ ኋላም መለሰን፤ ሕሊናችንን አስቶ ቀኑን ሙሉ ሰውነታችን እንዲዝል አደረገ።


ፍርሀትና ውድቀት እንዲሁም ጥፋትና ውድመት በእኛ ላይ ደረሱ።


በከለዳውያን ምድር በኬባር ወንዝ አጠገብ የእግዚአብሔር ቃል የቡዚ ልጅ ወደ ሆንኩት ወደ ካህኑ ወደ እኔ ወደ ሕዝቅኤል መጣ፤ የእግዚአብሔርም ኀይል በእኔ ላይ ነበረ።


የምትሄድበትን ስፍራ እንዳታይ ዕቃህን በትከሻህ ተሸክመህ ፊትህን በመሸፈን በጨለማ ስትሄድ ይመልከቱህ፤ እኔም ለእስራኤላውያን ምልክት አድርጌሃለሁ።”


“ልዑል እግዚአብሔር ሕያው አምላክ እንደ መሆኔ ይህ ንጉሥ በዙፋን ላይ ካስቀመጠው ከባቢሎን ንጉሥ ጋር በመሐላ የገባውን የስምምነት ውል በማፍረሱ ምክንያት በባቢሎን ይሞታል።


መረቤን በእርሱ ላይ ዘርግቼ በወጥመድ እንዲያዝ አደርጋለሁ፤ በእኔ ላይ ስለ ፈጸመው ክሕደት ወደ ባቢሎን አምጥቼ እፈርድበታለሁ።


ብዙ አሕዛብ በሚሰበሰቡበት ጊዜ መረቤን እዘረጋብሃለሁ፤ በእኔ መረብ መሳቢያም ጐትተው ወደ ዳር እንዲያወጡህ አደርጋለሁ።


በሚዘዋወሩበት ቦታ ሁሉ ወጥመዴን ዘርግቼ እንደ ወፍ እይዛቸዋለሁ፤ ስለ ሠሩትም ክፉ ሥራ እቀጣቸዋለሁ።


ያ ቀን በምድር ላይ የሚገኙትን ሰዎች ሁሉ በድንገት ያጠምዳቸዋል።


跟着我们:

广告


广告