Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 11:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 “ስለዚህ እኔ እግዚአብሔር የምለውን ሁሉ ንገራቸው፤ እነሆ፥ ከሕዝቦች መካከልና ከተበታተናችሁባቸው አገሮች እሰበስባችኋለሁ፤ የእስራኤልንም ምድር እንደገና እሰጣችኋለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “ስለዚህ እንዲህ በል፤ ‘ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ከአሕዛብ መካከል እሰበስባችኋለሁ፤ ከተበተናችሁባቸው አገሮች እመልሳችኋለሁ፤ የእስራኤልንም ምድር እንደ ገና እሰጣችኋለሁ።’

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ስለዚህ እንዲህ በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከሕዝቦች መካከል እሰበስባችኋለሁ፥ ከተበተናችሁባቸው አገሮችም እሰበስባችኋለሁ፥ የእስራኤልንም ምድር ለእናንተ እሰጣችኋለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ስለ​ዚ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ እቀ​በ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከበ​ተ​ን​ሁ​ባ​ቸ​ውም ሀገ​ሮች እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ምድር እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ስለዚህም በል፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከአሕዛብ ዘንድ አከማቻችኋለሁ ከተበተናችሁባቸውም አገሮች እሰበስባችኋለሁ፥ የእስራኤልንም ምድር እሰጣችኋለሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 11:17
27 交叉引用  

ከባዕድም አገር መልሶ አምጥቶአችኋል፤ ከምሥራቅና ከምዕራብ፥ ከሰሜንና ከደቡብ ሰብስቦአችኋል።


ሕዝብሽ ጻድቃን ይሆናሉ፤ ምድሪቱን ለዘለዓለም ይወርሳሉ፤ እኔ እመሰገን ዘንድ እነርሱን የፈጠርኳቸውና የተካኋቸው እኔ ነኝ።


“እኔ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ወደ ባቢሎን የላክኋቸውን ሕዝብ እንደነዚህ ጥሩ የበለስ ፍሬዎች እንደ ሆኑ እቈጥራለሁ፤


ለሕይወታቸውም በመጠንቀቅ ወደዚህች ምድር እንዲመለሱ አደርጋለሁ፤ አንጻቸዋለሁ፤ አላፈርሳቸውም፤ እተክላቸዋለሁ፤ አልነቅላቸውም፤


እኔ እግዚአብሔር መሆኔን እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ። ከዚያ በኋላም በሙሉ ልባቸው ወደ እኔ ስለሚመለሱ፥ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በባቢሎን የምትኖሩበት ሰባው ዓመት ከተፈጸመ በኋላ እንደገና እናንተን በምሕረት እጐበኛለሁ፤ ወደ አገራችሁ እንድመልሳችሁ የገባሁትን ቃል ኪዳን እፈጽማለሁ፤


ስለዚህም እግዚአብሔር ወደ ሰሜን ሄጄ ለእስራኤል እንድነግራት ያዘዘኝ ይህ ነው፤ “እምነት የማይጣልብሽ እስራኤል ሆይ! ወደ እኔ ተመለሺ፤ እኔ ምሕረቴ የበዛ ስለ ሆነ አልቈጣም፤ በአንቺ ላይ የምቈጣውም ለዘለዓለም አይደለም።


እስራኤልና ይሁዳ አንድ ይሆናሉ፤ ሁለቱም በአንድነት በስተሰሜን ካለው አገር ከምርኮ ይመለሳሉ፤ ለቀድሞ አባቶቻችሁ የዘለዓለም ርስት አድርጌ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ተመልሰው ይገባሉ።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የእስራኤልን ልጆች ቤት መልሼ እሠራለሁ፤ ለያንዳንዱም ቤተሰብ ምሕረቴን እልካለሁ፤ የኢየሩሳሌም ከተማ እንደገና ትሠራለች፤ ቤተ መንግሥቱም በድሮ ቦታ ተመልሶ ይታነጻል።


ለቅሶአችሁን አቁማችሁ እንባችሁን ጥረጉ፤ ስለ ልጆቻችሁ ያደረጋችኹት ነገር ሁሉ ያለ ዋጋ አይቀርም፤ እነርሱ ከጠላት አገር ተመልሰው ይመጣሉ።


ከተበታተናችሁባቸው አገሮችና ከሕዝቦች መካከል እሰበስባችኋለሁ፤ የምሰበስባችሁም በኀይሌና ሥልጣኔ፥ በማወርደው ቊጣዬ ነው።


ተበታትናችሁ ከነበራችሁባቸው አገሮች ሕዝቦች መካከል አውጥቼ በምሰበስባችሁ ጊዜ መልካም መዓዛ እንዳለው ዕጣን እቀበላችኋለሁ። ሌሎች ሕዝቦች እያዩ በእናንተ መካከል ቅድስናዬን እገልጣለሁ።


ለቀድሞ አባቶቻችሁ እንደምሰጣቸው ቃል ወደገባሁላቸው ምድር ወደ እስራኤል መልሼ በማመፃችሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እስራኤላውያን ከተበታተኑበት ከተለያዩ አሕዛብ መካከል በምሰበሰብበት ጊዜና ሌሎች ሕዝቦች እያዩ ቅድስናዬን በሕዝቤ መካከል በምገልጥበት ጊዜ ተመልሰው ለአገልጋዬ ለያዕቆብ በሰጠሁት በገዛ ምድራቸው ይኖራሉ።


“ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘እኔ ራሴ በጎቼን እፈልጋለሁ፤ በጥንቃቄም እጠብቃቸዋለሁ፤


ከሕዝቦችና ከሀገሮች ሰብስቤ በማውጣት ወደ ሀገራቸው አመጣቸዋለሁ፤ በመኖሪያ ቦታዎችና ውሃ በሚወርድበት ቦታ ሁሉ በእስራኤል ተራራዎች ላይ እመግባቸዋለሁ።


ከመንግሥቶች ከአገሮች ሁሉ አውጥቼ በመሰብሰብ ወደ ገዛ ምድራችሁ እመልሳችኋለሁ።


እኔ ሕዝቤን በስደት ከሚኖሩበት ከምሥራቅና ከምዕራብ አገር እታደጋቸዋለሁ፤


አምላክህ እግዚአብሔር ምሕረት ያደርግልሃል፤ በአሕዛብ መካከል አንተን ከበታተነበት ስፍራ ሁሉ መልሶ በማምጣት እንደገና ያበለጽግሃል።


跟着我们:

广告


广告