Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 11:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ስለዚህም በገዛ አገራችሁ ድንበር ላይ በጦርነት ትገደላላችሁ፤ በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በሰይፍ ትወድቃላችሁ፤ በእስራኤል ድንበር ላይ እፈርድባችኋለሁ፤ በዚያ ጊዜም እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በሰይፍ ትወድቃላችሁ፥ በእስራኤልም ድንበር እፈርድባችኋለሁ፥ እኔም ጌታ እንደሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በሰ​ይፍ ትወ​ድ​ቃ​ላ​ችሁ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ተራ​ሮች እፈ​ር​ድ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ሆንሁ ታው​ቃ​ላ​ችሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በሰይፍ ትወድቃላችሁ በእስራኤልም ድንበር እፈርድባችኋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 11:10
15 交叉引用  

በዚያም በቤተ መቅደሱ ሰሎሞንና የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ሰባት ቀን ሙሉ የዳስ በዓል አክብረው ሰነበቱ፤ በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ አንሥቶ በስተ ደቡብ እስከ ግብጽ ድንበር ድረስ ካለው ምድር ሁሉ የመጣው ሕዝብ እጅግ ብዙ ነበር፤


ቀድሞ የእስራኤል ይዞታ የነበረውን በስተ ሰሜን ከሐማት መተላለፊያ ጀምሮ በስተ ደቡብ እስከ ሙት ባሕር የሚገኘውን ግዛት ሁሉ ድል ነሥቶ እንደገና አስመለሰ፤ ይህም ሁሉ የተፈጸመው በጋትሔፌር ተወላጅ አገልጋይ በሆነው በአሚታይ ልጅ በነቢዩ ዮናስ አማካይነት የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር በሰጠው የተስፋ ቃል መሠረት ነው።


እግዚአብሔር በእውነተኛ ፍርዱ ተገለጠ፤ ክፉ ሰዎችም በክፉ ሥራቸው ወጥመድ ተያዙ።


ይኸውም በሪብላ ንጉሥ ሴዴቅያስ ዐይኑ እያየ ልጆቹ እንዲገደሉ ተደረገ፤ የይሁዳ ባለሥልጣኖችም ሁሉ ሞት ተፈረደባቸው።


አንድ ሰው መመካት ካለበት በምድር ላይ ምሕረትን፥ ትክክለኛ ፍርድንና እውነትን የማስገኝ እኔ አምላክ መሆኔን በመረዳት ይመካ፤ እኔም ደስ የሚያሰኘኝ ይኸው ነው፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


መሠረት ተጋልጦ ከምድር ወለል ጋር እስኪስተካከል ድረስ በቀለም የቀባችሁትን ግድግዳ አፍርሼ እጥለዋለሁ፤ ግድግዳው በሚወድቅበት ጊዜ እናንተም በውስጡ ትጠፋላችሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።


መሸፈኛ ሻሻችሁን ቀድጄ ሕዝቤን ከእጃችሁ አድናለሁ፤ ዳግመኛ በእናንተ እጅ አይወድቁም፤ እናንተም እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።


ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲያ ሐሰተኛ ራእይ አታዩም፤ የሟርተኝነትንም ሥራ አትሠሩም፤ ሕዝቤን ከእጃችሁ አድናለሁ፤ በዚያን ጊዜ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።”


ሐሰተኛ ራእይ በሚያዩና ሟርትን በሚያሟርቱ ነቢያት ላይ እጄን አነሣለሁ፤ እነርሱ በሕዝቤ ማኅበር ውስጥ አይገኙም፤ እንዲያውም በእስራኤል ሕዝብ መዝገብ ውስጥ አይመዘገቡም፤ ወደ እስራኤል ምድርም አይገቡም፤ በዚያን ጊዜ እኔ ልዑል እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።


የተገደሉት በአካባቢያችሁ ይጣላሉ፤ ከዚያ በኋላ እናንተ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን ታውቃላችሁ።


የጌባላውያን ምድርና ከምሥራቅ በአርሞንኤም ተራራ ደቡብ ከሚገኘው ከባዓልጋድ ተነሥቶ እስከ ሐማት መተላለፊያ ያለው መላው ሊባኖስ ገና አልተያዘም።


跟着我们:

广告


广告