Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 10:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እኔም ይህን በመመልከት ላይ ሳለሁ፥ ኪሩቤል ክንፎቻቸውን ዘርግተው ከመሬት ወደ ላይ በሚወጡበት ጊዜ ከጐናቸው የነበሩትም መንኰራኲሮቹ አብረዋቸው ሲወጡ አየሁ፤ በቤተ መቅደሱ በስተ ምሥራቅ ባለው የቅጽር በር ሲደርሱ ቆሙ፤ የእስራኤል አምላክም ክብር በእነርሱ ላይ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ኪሩቤልም እኔ እያየኋቸው ክንፎቻቸውን ዘርግተው ከምድር ተነሥተው ሄዱ፤ መንኰራኵሮቹም ዐብረዋቸው ሄዱ፤ በእግዚአብሔርም ቤት በምሥራቁ በር መግቢያ ላይ ቆሙ፤ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ፥ እኔም እያየሁ ከምድር ተነሡ፥ ሲወጡም መንኰራኵሮች በአጠገባቸው ነበሩ፥ በጌታ ቤት በምሥራቁ በር መግቢያ ቆሙ፥ የእስራኤል አምላክ ክብርም በላያቸው ላይ ነበረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ኪሩ​ቤ​ልም ክን​ፎ​ቻ​ቸ​ውን ዘረጉ፤ እኔም እያ​የሁ ከም​ድር በረሩ፤ በወ​ጡም ጊዜ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮቹ በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው ነበሩ፤ፊት ለፊት በአ​ለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት መግ​ቢያ በር ዳርቻ ቆሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ክብር ከእ​ነ​ርሱ ጋራ በላ​ያ​ቸው ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ኪሩቤልም ክንፎቻቸውን ዘረጉ እኔም እያየሁ ከምድር ከፍ ከፍ አሉ፥ በወጡም ጊዜ መንኰራኵሮች በአጠገባቸው ነበሩ፥ በእግዚአብሔርም ቤት በምሥራቁ በር መግቢያ ቆሙ፥ የእስራኤልም አምላክ ክብር በላያቸው ላይ ነበረ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 10:19
9 交叉引用  

ከኪሩቤል ራሶች በላይ ያለውን ጠፈር ተመለከትኩ፤ በኪሩቤል ላይ ከሰንፔር ዕንቊ የተሠራ ዙፋን የሚመስል ነገር አየሁ።


የእግዚአብሔር መንፈስ ከምድር ወደ ላይ አንሥቶ በምሥራቅ ትይዩ ወደ ሆነው በእግዚአብሔር ቤት ወደ አለው ወደ ምሥራቁ በር አመጣኝ፤ እዚያም በቅጽር በሩ አጠገብ ኻያ አምስት ሰዎችን አየሁ፤ በእነርሱም መካከል የሕዝብ መሪዎች የሆኑት የዐዙር ልጅ አዛንያና የበናያ ልጅ ፈላጥያ ይገኙባቸዋል።


ያ ሰው በምሥራቅ አቅጣጫ ወደሚገኘው የቅጽር በር ወሰደኝ፤


እዚያም የእስራኤል አምላክ ክብር ከወደ ምሥራቅ እየተገለጠ ነበር፤ ድምፁም እንደ ኀይለኛ የውሃ ማዕበል ነበር፤ የክብሩ ነጸብራቅም በምድር ላይ አበራ።


የእግዚአብሔር ክብር በምሥራቁ የቅጽር በር በኩል አልፎ ወደ ቤተ መቅደሱ ገባ።


ስለዚህ በውስጥ በኩል ወዳለው ወደ ቤተ መቅደሱ አደባባይ ወሰደኝ፤ እዚያም ወደ መቅደሱ መግቢያ አጠገብ በመሠዊያውና በመተላለፊያው መካከል ኻያ አምስት ያኽል ሰዎች ነበሩ፤ እነርሱም ጀርባቸውን ወደ መቅደሱ አድርገው የምትወጣዋን ፀሐይ በማምለክ ወደ ምሥራቅ ተንበርክከው ይሰግዱ ነበር።


跟着我们:

广告


广告