Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 10:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ኪሩቤል ወደ ላይ ተነሡ እነርሱም በኬባር ወንዝ አጠገብ ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረቶች ናቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ኪሩቤልም ወደ ላይ ተነሡ፤ እነዚህም በኮቦር ወንዝ አጠገብ ያየኋቸው ሕያዋን ፍጡራን ነበሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ኪሩቤልም ተነሡ፥ እነዚህ በኮቦር ወንዝ ያየኋቸው ሕያዋን ናቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 እነ​ዚ​ህም በኮ​ቦር ወንዝ በእ​ን​ስ​ሶች አም​ሳል ያየ​ኋ​ቸው ኪሩ​ቤል በረሩ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ኪሩቤልም ከፍ ከፍ አሉ፥ ይህ በኮቦር ወንዝ ያየሁት እንስሳ ነው።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 10:15
10 交叉引用  

በሠላሳኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን በኬባር ወንዝ አጠገብ በአይሁድ ምርኮኞች መካከል ሳለሁ ሰማያት ተከፍተው የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።


በከለዳውያን ምድር በኬባር ወንዝ አጠገብ የእግዚአብሔር ቃል የቡዚ ልጅ ወደ ሆንኩት ወደ ካህኑ ወደ እኔ ወደ ሕዝቅኤል መጣ፤ የእግዚአብሔርም ኀይል በእኔ ላይ ነበረ።


በዐውሎ ነፋሱም መካከል የሰው መልክ ያላቸው አራት ሕያዋን ፍጥረቶች አየሁ፤


ኪሩቤሉ ሲንቀሳቀሱ ከጐናቸው ያሉት መንኰራኲሮችም አብረው ይንቀሳቀሳሉ፤ ኪሩቤሉ ለመነሣት ክንፋቸውን ሲዘረጉ ከጐናቸው ያሉት መንኰራኲሮችም ወደ ሌላ አይዞሩም።


በዚህ ጊዜ ኪሩቤል ክንፎቻቸውን ዘርግተው መብረር ጀመሩ፤ መንኰራኲሮቹም ከጐናቸው ነበሩ፤ የእስራኤል አምላክ አንጸባራቂ ክብር ከበላያቸው ነበር፤


ይህም ራእይ ከዚህ በፊት እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን ለማጥፋት በመጣ ጊዜ ያየሁትን ይመስል ነበር፤ በኬባር ወንዝ አጠገብ ካየሁትም ራእይ ጋር ይመሳሰላል፤ በዚያን ጊዜ በግንባሬ ተደፋሁ።


እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ! የሆነውን ነገር ሁሉ ታያለህን? የእስራኤል ሕዝብ በዚህ ስፍራ የሚፈጽሙትን አጸያፊ ነገር ተመልከት፤ በዚህ አድራጎታቸው ከተቀደሰው ስፍራዬ እንድርቅ አድርገውኛል፤ ከዚህም የበለጠ እጅግ አስነዋሪ የሆነ ነገር ገና ታያለህ።”


ልጆች ወልደው ቢያሳድጉም ሁሉንም ስለምቀሥፋቸው ልጅ አልባ ሆነው ይቀራሉ፤ እኔ ከእነርሱ በራቅሁ ጊዜ ወዮላቸው!”


跟着我们:

广告


广告