Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 10:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከኪሩቤል ራሶች በላይ ያለውን ጠፈር ተመለከትኩ፤ በኪሩቤል ላይ ከሰንፔር ዕንቊ የተሠራ ዙፋን የሚመስል ነገር አየሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እኔም አየሁ፤ እነሆ ከኪሩቤል ራስ በላይ ካለው ጠፈር ከፍ ብሎ፣ የሰንፔር ዙፋን የሚመስል ነገር ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እኔም አየሁ፥ እነሆ ከኪሩቤል ራስ በላይ ካለው ጠፈር ከፍ ብሎ እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ፥ ዙፋን የሚመስል ነገር ታየ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እኔም አየሁ፤ እነ​ሆም በኪ​ሩ​ቤል ራስ ላይ ባለው ጠፈር በላ​ያ​ቸው እንደ ሰን​ፔር ድን​ጋይ ያለ ዙፋን የሚ​መ​ስል መልክ ተገ​ለጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እኔም አየሁ፥ እነሆም፥ በኪሩቤል ራስ ላይ ባለው ጠፈር በላያቸው እንደ ሰንፔር ድንጋይ ያለ እንደ ዙፋን የሚመስል መልክ ተገለጠ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 10:1
27 交叉引用  

እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦ “እኔ የማደርገውን ነገር ከአብርሃም እሰውረዋለሁን?


ቀና ብሎም ሲመለከት ሦስት ሰዎች እዚያ ቆመው አየ፤ እንዳያቸውም ወዲያውኑ ሊያነጋግራቸው ወደ እነርሱ ሮጠ፤ ግንባሩም መሬት እስኪነካ ዝቅ ብሎ በመስገድ እጅ ነሣ፤


ከዚህ በኋላ ሁለቱ ሰዎች ወደ ሰዶም ለመሄድ ተነሡ፤ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት እንደ ቆመ ቈየ፤


አብርሃምም “ጌታ ሆይ፥ አሁንም እንደገና በመናገሬ ይቅር በለኝ፤ ምናልባት ኻያ ቢገኙስ?” አለ፤ እግዚአብሔርም “ኻያ ቢገኙ ለእነርሱ ስል ከተማይቱን አላጠፋም” አለ።


አዳምንም ካስወጣው በኋላ ከዔደን የአትክልት ቦታ በስተ ምሥራቅ በኩል ኪሩቤል የተባሉትን መላእክትንና በየአቅጣጫው እየተገለባበጠ እንደ እሳት የሚንበለበለውን ሰይፍ አኖረ፤ ይህንንም ያደረገው ማንም ወደ ሕይወት ዛፍ እንዳይጠጋ ነው።


እርሱ ግን በስተማዶ ለብቻው ቀረ፤ ከዚህ በኋላ ሌሊቱ እስኪነጋ ድረስ አንድ ሰው ሲታገለው ዐደረ።


ያዕቆብም “እኔ እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አይቼ እነሆ፥ በሕይወት እገኛለሁ” አለ። በዚህም ምክንያት ያንን ቦታ “ጵንኤል” ብሎ ጠራው።


በኪሩቤል ላይ ሆኖ በረረ፤ በነፋስ ክንፎች ላይ ሆኖ ወደ ላይ መጠቀ።


የእስራኤልንም አምላክ አዩ፤ በእግሮቹ ሥር ከብሩህ ሰንፔር የተሠራና የሚያበራ ሰማይ የሚመስል ወለል ነበር።


ከብዙ ቀኖች በኋላም እግዚአብሔር፥ “ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ተመልሰህ ሂድና መታጠቂያውን ውሰድ” አለኝ።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦


በሠላሳኛው ዓመት፥ በአራተኛው ወር፥ ከወሩም በአምስተኛው ቀን በኬባር ወንዝ አጠገብ በአይሁድ ምርኮኞች መካከል ሳለሁ ሰማያት ተከፍተው የእግዚአብሔርን ራእይ አየሁ።


እነዚህም በኬባር ወንዝ አጠገብ ከእስራኤል አምላክ ሥር ያየኋቸው ሕያዋን ፍጥረቶች ናቸው፤ እኔም ኪሩቤል መሆናቸውን ዐወቅሁ።


በዚህ ጊዜ ኪሩቤል ክንፎቻቸውን ዘርግተው መብረር ጀመሩ፤ መንኰራኲሮቹም ከጐናቸው ነበሩ፤ የእስራኤል አምላክ አንጸባራቂ ክብር ከበላያቸው ነበር፤


ከዚህ በኋላ ያ በፍታ የለበሰውና የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር የያዘው ሰው ተመልሶ መጥቶ “ያዘዝከኝን ሁሉ ፈጽሜአለሁ” ብሎ ለእግዚአብሔር ተናገረ።


በጥበቃ ቦታዬ እቆማለሁ በግንቡ ጫፍ ላይም ቦታዬን እይዛለሁ፤ እግዚአብሔር ምን እንደሚለኝ ለጥያቄዬም ምን መልስ እንደሚሰጥ እጠባበቃለሁ።


እግዚአብሔርን ያየው ከቶ ማንም የለም፤ ይሁን እንጂ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ያለው አንድያ ልጁ ብቻ ገለጠው።


እግዚአብሔር ኢያሱን እንዲህ አለው፤ “ኢያሪኮን ከንጉሥዋና ከወታደሮችዋ ጋር በእጅህ አሳልፌ እሰጥሃለሁ፤


እርሱ ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ ነው፤ መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ተገዝተውለታል።


በመቅረዞቹ መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፤ እርሱ እስከ እግሩ የሚደርስ ረጅም ልብስ የለበሰ፥ ደረቱን በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበረ።


跟着我们:

广告


广告