Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 1:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 የእያንዳንዱ ፍጥረት ሁለት ክንፎች ግራና ቀኝ ተዘርግተው ጫፎቻቸው ይነካካሉ፤ ስለዚህ ሰውነታቸው ወዲያና ወዲህ ሳይል በኅብረት ይንቀሳቀሱ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ክንፎቻቸውም እርስ በርስ ይነካኩ ነበር። እያንዳንዱም ቀጥ ብሎ ይሄድ ነበር፤ ወደ ኋላቸውም ዞር ብለው አይመለከቱም ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ክንፎቻቸው እርስ በእርሱ ይነካካ ነበር፥ ሲሄዱም አይዞሩም፥ እያንዳንዱም ቀጥ ብሎ ይሄድ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 የሁ​ሉም ክን​ፎ​ቻ​ቸው አንዱ ከአ​ንዱ ጋር የተ​ያ​ያዘ ነው፤ ሲሄ​ዱም ወዲ​ያና ወዲህ ሳይሉ አቅ​ን​ተው ይሄ​ዳሉ፤ አን​ዱም አን​ዱም ወደ​ፊቱ ይሄ​ዳል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ክንፎቻቸው እርስ በእርሱ የተያያዘ ነበረ፥ ሲሄዱም አይገላምጡም ነበረ፥ እያንዳንዱም ፊቱን አቅንቶ ይሄድ ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 1:9
9 交叉引用  

እነርሱም ከአራቱ አቅጣጫዎች ወደፈለጉት አቅጣጫ ወደ ሌላ ሳይዞሩ ቀጥ ብለው ይሄዳሉ።


ወደ ፊታቸው በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ ወደ የትኛውም አቅጣጫ ሳይዞሩ በቀጥታ ይሄዳሉ፤ የፊቱ መንኰራኲር ወደ የትኛውም አቅጣጫ ቢሄድ ሌሎቹ ሳይዞሩ በቀጥታ ይከተላሉ።


ፊቶቻቸውም እነዚያኑ በኬባር ወንዝ አጠገብ ያየኋቸውን ፊቶች ይመስሉ ነበር፤ እያንዳንዱም ኪሩብ በቀጥታ ወደ ፊት ይሄድ ነበር።


ኢየሱስ የሚያርግበት ቀን በተቃረበ ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ለመሄድ ቈርጦ ተነሣ።


ኢየሱስም “ለማረስ በእጁ ዕርፍ ይዞ ወደ ኋላ የሚመለከት ሰው ለእግዚአብሔር መንግሥት የተገባ አይደለም፤” ሲል መለሰለት።


ወንድሞቼ ሆይ! “መለያየት በመካከላችሁ አይኑር፤ ሁላችሁም ተስማምታችሁ በአንድ ሐሳብና በአንድ ዓላማ ጸንታችሁ ኑሩ” ብዬ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።


跟着我们:

广告


广告