Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 1:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 የፍጥረቶቹ መንፈስ በመንኰራኲሮቹም ውስጥ በመኖሩ ፍጥረቶቹ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ አብረው ይንቀሳቀሳሉ፤ ሲቆሙም አብረው ይቆማሉ፤ ከመሬት ወደ አየር በሚመጥቁበትም ጊዜ፥ አብረው ይመጥቃሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ፍጡራኑ ሲንቀሳቀሱ ይንቀሳቀሳሉ፤ ፍጡራኑ ቀጥ ብለው ሲቆሙ እነርሱም ይቆማሉ፤ ፍጡራኑ ከምድር ከፍ ከፍ ሲሉ፣ የሕያዋኑ ፍጡራን መንፈስ በውስጣቸው ስላለ መንኰራኵሮቹ ዐብረዋቸው ይነሣሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 የሕያዋኑ መንፈስ በመንኮራኩሮቹ ውስጥ ስለ ነበረ ሲሄዱ ይሄዳሉ፥ ሲቆሙ ይቆማሉ፥ ከምድር ሲነሡ መንኮራኩሮቹም በአጠገባቸው ይነሣሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 በሄ​ዱም ጊዜ ይሄ​ዳሉ፤ በቆ​ሙም ጊዜ ይቆ​ማሉ፤ በእ​ነ​ዚያ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮች ውስጥ የሕ​ይ​ወት መን​ፈስ አለና ከም​ድር በተ​ነሡ ጊዜ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮቹ ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይነ​ሣሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 የእንስሶች መንፈስ በመንኰራኵሮቹ ውስጥ ነበረና እነዚያ ሲሄዱ እነዚህ ይሄዱ ነበር፥ እነዚያም ሲቆሙ እነዚህ ይቆሙ ነበር፥ እነዚያም ከምድር ከፍ ከፍ ሲሉ መንኰራኵሮቹ በአጠገባቸው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 1:21
4 交叉引用  

ከሕያዋን ከፍጥረቶቹ ራስ በላይ እንደ መስተዋት ከሚያብረቀርቅ የከበረ ድንጋይ የተሠራ ጠፈር የሚመስል ወለል ነበር።


የሕያዋን ፍጥረቶች መንፈስ በመንኰራኲሮቹ ውስጥ ስላለ ፍጥረቶቹ ሲቆሙ መንኰራኲሮቹም አብረው ይቆማሉ፤ ኪሩቤሉ ሲነሡ መንኰራኲሮቹም ወደ ሌላ አይዞሩም።


በኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኘውን ሕይወት የሚሰጥ የመንፈስ ቅዱስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ ነጻ አውጥቶኛል።


跟着我们:

广告


广告