Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 1:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ፍጥረቶቹ በተንቀሳቀሱ ቊጥር መንኰራኲሮቹ አብረዋቸው ይንቀሳቀሱ ነበር፤ ፍጥረቶቹ ከምድር ተነሥተው ከፍ በሚሉበትም ጊዜ መንኰራኲሮቹ አብረው ከፍ ይሉ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ሕያዋኑ ፍጡራን ሲንቀሳቀሱ፣ በአጠገባቸው ያሉ መንኰራኵሮችም ይንቀሳቀሱ ነበር፤ ሕያዋኑ ፍጡራን ከምድር ከፍ ከፍ ሲሉ፣ መንኰራኵሮቹም ዐብረዋቸው ከፍ ከፍ ይሉ ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ሕያዋኑም ሲሄዱ መንኮራኩሮቹም በአጠገባቸው ይሄዱ ነበር። እንስሶቹ ከምድር ሲነሱ መንኮራኩሮቹም ይነሱ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 በሄ​ዱም ጊዜ ሠረ​ገ​ላ​ዎች ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይሄ​ዳሉ። እን​ስ​ሶ​ቹም ከም​ድር ሲነሡ መን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ይነ​ሣሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እንስሶቹም በሄዱ ጊዜ መንኰራኵሮቹ በአጠገባቸው ሄዱ። እንስሶቹም ከምድር ከፍ ከፍ ባሉ ጊዜ መንኰራኵሮቹ ከፍ ከፍ አሉ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 1:19
5 交叉引用  

ትእዛዞቹን የምትፈጽሙ የሚናገረውን የምታዳምጡ፤ እናንተ ኀያላንና ብርቱዎች መላእክቱ እግዚአብሔርን አመስግኑ።


አራቱን ፍጥረቶች በመመልከት ላይ ሳለሁ፥ አራት መንኰራኲሮች ወደ መሬት ተሽከርክረው ሲወርዱና በሕያዋን ፍጥረቶቹ አጠገብ ጐን ለጐን በተርታ ሲቀመጡ አየሁ፤


የፍጥረቶቹ መንፈስ በመንኰራኲሮቹም ውስጥ በመኖሩ ፍጥረቶቹ በሚንቀሳቀሱበት ጊዜ አብረው ይንቀሳቀሳሉ፤ ሲቆሙም አብረው ይቆማሉ፤ ከመሬት ወደ አየር በሚመጥቁበትም ጊዜ፥ አብረው ይመጥቃሉ።


ኪሩቤሉ ሲንቀሳቀሱ ከጐናቸው ያሉት መንኰራኲሮችም አብረው ይንቀሳቀሳሉ፤ ኪሩቤሉ ለመነሣት ክንፋቸውን ሲዘረጉ ከጐናቸው ያሉት መንኰራኲሮችም ወደ ሌላ አይዞሩም።


እኔም ይህን በመመልከት ላይ ሳለሁ፥ ኪሩቤል ክንፎቻቸውን ዘርግተው ከመሬት ወደ ላይ በሚወጡበት ጊዜ ከጐናቸው የነበሩትም መንኰራኲሮቹ አብረዋቸው ሲወጡ አየሁ፤ በቤተ መቅደሱ በስተ ምሥራቅ ባለው የቅጽር በር ሲደርሱ ቆሙ፤ የእስራኤል አምላክም ክብር በእነርሱ ላይ ነበር።


跟着我们:

广告


广告