Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ሕዝቅኤል 1:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 አራቱን ፍጥረቶች በመመልከት ላይ ሳለሁ፥ አራት መንኰራኲሮች ወደ መሬት ተሽከርክረው ሲወርዱና በሕያዋን ፍጥረቶቹ አጠገብ ጐን ለጐን በተርታ ሲቀመጡ አየሁ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ሕያዋን ፍጡራኑን ስመለከታቸው፣ አራት ፊቶች ባሉት በእያንዳንዱ ፍጡር አጠገብ አንዳንድ መንኰራኵር በምድር ላይ አየሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ሕያዋኑንም ስመለከት፥ እነሆ፥ በአራቱ ሕያዋን አጠገብ በምድር ላይ ለእያንዳንዳቸው አንድ አንድ መንኰራኵር አየሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ስመ​ለ​ከ​ትም፥ እነሆ በአ​ራቱ እን​ስ​ሶች አጠ​ገብ በም​ድር ላይ አንድ መን​ኰ​ራ​ኵር አየሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 እንስሶችንም ስመለከት፥ እነሆ፥ በአራቱ እንስሶች አጠገብ በምድር ላይ አንድ አንድ መንኰራኵር አየሁ።

参见章节 复制




ሕዝቅኤል 1:15
9 交叉引用  

እያንዳንዱ የዕቃ ማስቀመጫ ከነሐስ የተሠሩ አራት መንኰራኲሮችና መንኰራኲሮቹ የሚሽከረከሩበት የነሐስ ወስከምቶች ነበራቸው፤ እንዲሁም በአራቱ ማእዘኖች የመታጠቢያ ገንዳ መደገፊያዎች ነበሩ፤ መደገፊያዎቹም የአበባ ጒንጒን በሚመስሉ ቅርጾች አጊጠው ነበር።


እያንዳንዱም ፍጥረት አራት አራት ፊትና አራት አራት ክንፍ ነበሩት።


እግዚአብሔርም ቀጭን ሐር የለበሰውን ሰው “ከሕያዋን ፍጥረቶች በታች ባሉት መንኰራኲሮች መካከል አልፈህ ሂድ፤ ከከሰልም ፍም በእጅህ አፍሰህ ውሰድና በከተማይቱ ላይ በትነው!” አለው። እኔም እያየሁት ገባ፤


ስመለከት እያንዳንዱ መንኰራኲር በያንዳንዱ ኪሩብ አጠገብ ሆኖ አራት መንኰራኲሮችን አየሁ፤ የመንኰራኲሮቹም መልክ የሚያንጸባርቅ ዕንቊ ይመስል ነበር።


የሕያዋን ፍጥረቶቹ ክንፎቹ እርስ በርሳቸው በአየር ላይ ሲፋጩ ሰማሁ፤ ከመንኰራኲሮቹም የሚሰማው የጋጋታ ድምፅ ከፍተኛ ነበር።


“እኔም እየተመለከትኩ ሳለሁ ዙፋኖች ተዘረጉ፤ ያ ጥንታዊው በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤ ልብሱ እንደ በረዶ፥ ጠጒሩም እንደ ነጭ ሱፍ ነበር፤ ዙፋኑና የዙፋኑ መንኰራኲር እንደሚነድ እሳት ይንበለበሉ ነበር።


የመጀመሪያው እንስሳ አንበሳ ይመስል ነበር፤ ሁለተኛው በሬ ይመስል ነበር፤ ሦስተኛው የሰው ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤ አራተኛው የሚበር ንስር ይመስል ነበር።


跟着我们:

广告


广告