Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 9:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እግዚአብሔር ግን በእስራኤላውያንና በግብጻውያን እንስሶች መካከል ልዩነት ያደርጋል፤ ከእስራኤላውያን እንስሶች አንድ እንኳ አይሞትም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ነገር ግን እግዚአብሔር በእስራኤልና በግብጽ እንስሳት መካከል ልዩነት ያደርጋል፤ ይኸውም የእስራኤል የሆነ ማንኛውም እንስሳ እንዳይሞት ነው።’ ”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ጌታም በእስራኤልና በግብጽ ከብቶች መካከል ይለያል፤ ከእስራኤልም ልጆች ከብት አንድ ስንኳ አይሞትም።’”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በዚያ ጊዜም በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ከብ​ቶ​ችና በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከብ​ቶች መካ​ከል ልዩ​ነት አደ​ር​ጋ​ለሁ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከብ​ቶች አን​ዳች አይ​ሞ​ትም።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እግዚአብሔርም በእስራኤልና በግብፅ ከብቶች መካከል ይለያል፤ ከእስራኤልም ልጆች ከብት አንዳች አይጠፋም።’”

参见章节 复制




ዘፀአት 9:4
10 交叉引用  

ግብጻውያን እርስ በርሳቸው ስለማይተያዩ ማንም ሰው እስከ ሦስት ቀን ከቤቱ መውጣት አልቻለም ነበር፤ እስራኤላውያን በሚኖሩበት ስፍራ ግን ብርሃን ነበር።


በደጃፎቻችሁ መቃኖች ላይ የሚታየው ደም እናንተ የምትኖሩባቸውን ቤቶች ለይቶ የሚያሳይ ምልክት ይሆናል፤ እኔም ደሙን በማይበት ጊዜ አልፌአችሁ እሄዳለሁ፤ በዚህም ዐይነት ግብጻውያንን በመቅሠፍት በምመታበት ጊዜ፥ በእናንተ ላይ ምንም ዐይነት መቅሠፍት አይደርስባችሁም።


አስማተኞቹም “ይህ የእግዚአብሔር ሥራ ነው!” ብለው ለንጉሡ ነገሩት፤ ንጉሡ ግን ልቡን አደነደነ፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረውም ሙሴንና አሮንን መስማት አልፈለገም።


ነገር ግን በዚህ ምድር መካከል እኔ እግዚአብሔር መገኘቴን ታውቅ ዘንድ በዚያን ቀን ሕዝቤ የሚኖርባትን የጌሴምን ምድር ከዝንቦቹ መንጋ ነጻ አድርጌ እለያታለሁ።


እስራኤላውያን በሚኖሩባት በጌሴም ምድር ብቻ በረዶ አልነበረም።


እግዚአብሔር ይህን ነገር ነገ አደርጋለሁ ብሎ ጊዜውን ወሰነ።’ ”


እግዚአብሔርም በተናገረው መሠረት በማግስቱ ይህንኑ አደረገ፤ የግብጻውያን እንስሶች ሁሉ አለቁ፤ ነገር ግን ከእስራኤላውያን እንስሶች አንድ እንኳ አልሞተም።


አዝመራችሁ ከመድረሱ ከሦስት ወር በፊት ዝናብ እንዲቋረጥ አደረግሁ፤ በአንድ ከተማ ሲዘንብ በሌላው ከተማ እንዳይዘንብ አደረግሁ፤ ለአንዱ እርሻ ሲዘንብለት ሌላው እርሻ ዝናብ አጥቶ ደረቀ።


በዚያን ጊዜ በጻድቅና በኃጢአተኛ ለእግዚአብሔር በሚታዘዝና በማይታዘዝ ሰው መካከል ያለውን ልዩነት እንደገና ታያላችሁ።”


跟着我们:

广告


广告