Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 9:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እግዚአብሔር በዚህና በዚያ ከሚራወጥ የመብረቅ ብልጭልጭታ ጋር ከባድ የበረዶ ዝናብ አወረደ፤ ይህም ዐይነቱ የበረዶ ዝናብ በግብጽ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 በረዶ ወረደ፤ መብረቅም አብረቀረቀ፤ ግብጽ አገር ከሆነችበት ዘመን አንሥቶ በምድሪቱ ሁሉ እንደዚህ ያለ አስከፊ ማዕበል ሆኖ አያውቅም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 በረዶና እሳት ነበረ፥ በበረዶውም መካከል እጅግ ከባድ የሚበርቅ እሳት ነበር፥ በግብጽ ምድር ሁሉ አገር ከሆነ ጀምሮ እንደ እርሱ ሆኖ አያውቅም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 በረ​ዶም ነበረ፤ በበ​ረ​ዶ​ውም መካ​ከል እሳት ይቃ​ጠል ነበር፤ በረ​ዶ​ውም በግ​ብፅ ሀገር ሁሉ ሕዝብ ከኖ​ረ​በት ጊዜ ጀምሮ እስ​ከ​ዚች ቀን እንደ እርሱ ያል​ሆነ እጅግ ብዙና ጠን​ካራ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 በረዶም ነበረ፤ በበረዶውም መካከል እሳት ይቃጠል ነበር፤ በረዶውም በግብፅ አገር ሁሉ ሕዝብ ከሆነ ጀምሮ እንደ እርሱ ያልሆነ እጅግ ታላቅ ነበረ።

参见章节 复制




ዘፀአት 9:24
11 交叉引用  

ይህም በረዶ እኔ በጦርነትና በውጊያ ላይ እንድጠቀምበት ለችግር ጊዜ ያስቀመጥኩት ነው።


እግዚአብሔር በአገራቸው ላይ በዝናብ ፈንታ የበረዶ ናዳንና መብረቅን አወረደ።


እግዚአብሔር ከሰማይ አንጐደጐደ፤ ልዑል እግዚአብሔር ድምፁን አሰማ።


ቤተ መንግሥትህን፥ የመኳንንትህንና የሕዝብህን ቤቶች ሁሉ የአንበጣ መንጋ ይሞላዋል፤ ይህም ሁኔታ ከቀድሞ አባቶችህ ዘመን እስከ አሁን ከታየው መከራ ሁሉ የከፋ ይሆናል።’ ” ሙሴም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ ሄደ።


እነሆ፥ ነገ በዚህ ጊዜ በግብጽ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ከባድ የበረዶ ዝናብ አመጣለሁ፤


ስለዚህ ሙሴ በትሩን አንሥቶ ወደ ሰማይ ዘረጋ፤ እግዚአብሔርም ነጐድጓድና በረዶ መብረቅም ወደ ምድር አወረደ፤ በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር በግብጽ ምድር ላይ በረዶን አዘነበ።


በረዶው በግብጽ ምድር ሁሉ በሜዳ የተገኘውን ማንኛውንም ነገር ሕዝቡንና እንስሶቹን ጭምር ጨፈጨፈ፤ በሜዳ ላይ ያለውን አትክልት ሁሉ መታ፤ ዛፎችንም ሁሉ ሰባበረ።


እግዚአብሔር ክቡር ድምፁን እንዲሰሙ ያደርጋል። በኀይለኛ ቊጣው፥ በሚያቃጥል የእሳት ነበልባል፥ በመብረቅ፥ በወጀብና በጠጣር በረዶ የሚወርደው ኀይለኛ ቅጣቱ እንዲታይ ያደርጋል።


ቀና ብዬ ስመለከት ብርቱ ዐውሎ ነፋስ ከሰሜን በኩል ሲመጣ አየሁ፤ ከግዙፍ ደመና የመብረቅ ብልጭታ ይታይ ነበር፤ በዙሪያው ያለውም ሰማይ ቀላ፤ መብረቁ በሚበርቅበትም ስፍራ አንዳች ነገር እንደ ነሐስ አበራ።


ስለዚህ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የኢየሩሳሌምን ቅጽር ለማጥፋት በቊጣዬ ዐውሎ ነፋስ እንዲነሣ አደርጋለሁ። ዶፍ ዝናብና የበረዶ ናዳ ይወርዳል።


በዚያን ጊዜ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ያልሆነ፥ ወደፊትም እርሱን የሚመስል ከቶ የማይሆን፥ ታላቅ መከራ ይሆናል።


跟着我们:

广告


广告