Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 9:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እነሆ፥ ነገ በዚህ ጊዜ በግብጽ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ከባድ የበረዶ ዝናብ አመጣለሁ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ስለዚህ ነገ በዚህ ጊዜ ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ድረስ በግብጽ ላይ ወርዶ የማያውቅ አስከፊ የበረዶ ማዕበል እልካለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 እነሆ እኔ ነገ በዚህ ጊዜ በግብጽ፥ ከተመሠረተች ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ ሆኖ የማያውቅ፥ እጅግ ከባድ በረዶ አዘንባለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 እነሆ፥ ከተ​መ​ሠ​ረ​ተች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ በግ​ብፅ ሆኖ የማ​ያ​ውቅ እጅግ ታላቅ በረዶ ነገ በዚህ ጊዜ አዘ​ን​ባ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 እነሆ ነገ በዚህ ጊዜ፥ ከተመሰረተች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ በግብፅ ሆኖ የማያውቅ፥ እጅግ ታላቅ በረዶ አዘንብብሃለሁ።

参见章节 复制




ዘፀአት 9:18
14 交叉引用  

ስለዚህ እርስዋ “በእነዚያ ነቢያት ላይ ያደረግኸውን እኔም ነገ ልክ በአሁኑ ሰዓት በአንተ ላይ ሳላደርግብህ ብቀር አማልክት በሞት ይቅሠፉኝ!” ስትል ወደ ኤልያስ የዛቻ መልእክት ላከች።


አሁን ደግሞ ቤተ መንግሥትህንና የባለሥልጣኖችህን ቤት ሁሉ በርብረው ዋጋ ያለውን ንብረት ሁሉ ይዘው እንዲመጡ የጦር መኰንኖቼን እልካለሁ፤ እነርሱም ነገ ጧት በዚሁ ሰዓት እዚያ ይደርሳሉ።”


ኤልሳዕም “እግዚአብሔር የሚለውን ስማ! ነገ ይህን ጊዜ በሰማርያ ሦስት ኪሎ ምርጥ ስንዴ ወይም ስድስት ኪሎ ገብስ በአንድ ጥሬ ብር ይሸመታል” ሲል መለሰለት።


በዚያን ጊዜ ኤልሳዕ ለንጉሡ “በነገው ዕለት በሰማርያ ከተማ ሦስት ኪሎ ምርጥ ስንዴ ወይም ስድስት ኪሎ ገብስ በአንድ ጥሬ ብር ይሸመታል” ብሎ ነግሮት ነበር፤


እግዚአብሔር ዝናብን የሚያዘንበው፥ ምድርን ለማረስረስ፥ ሰዎችን ለመቅጣት፥ ወይም ፍቅሩን ለመግለጥ ነው።


“ወደ በረዶ ማስቀመጫ ቤት ገብተሃልን? ወይስ የተቀመጠውን የበረዶ ክምችት አይተሃልን


ይህም በረዶ እኔ በጦርነትና በውጊያ ላይ እንድጠቀምበት ለችግር ጊዜ ያስቀመጥኩት ነው።


በሞገድህ አባራቸው፤ በዐውሎ ነፋስህም አስደንግጣቸው።


እነርሱም በመርመስመስ መጥተው አገሪቱን ወረሩ፤ ይህን ያኽል ብዛት ያለው የአንበጣ መንጋ ከዚያ በፊት ታይቶ አይታወቅም፤ ወደ ፊትም ሊታይ አይችልም።


ቤተ መንግሥትህን፥ የመኳንንትህንና የሕዝብህን ቤቶች ሁሉ የአንበጣ መንጋ ይሞላዋል፤ ይህም ሁኔታ ከቀድሞ አባቶችህ ዘመን እስከ አሁን ከታየው መከራ ሁሉ የከፋ ይሆናል።’ ” ሙሴም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ ሄደ።


በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ከዚህ በፊት ያልነበረ ወደ ፊትም የማይኖር ታላቅ ለቅሶ ይሆናል።


አንተ እስከ አሁንም በሕዝቤ ላይ ታብየሃል፤ እንዲሄዱም አልፈቀድክላቸውም።


እያንዳንዱ አርባ አምስት ኪሎ ግራም ያኽል የሚመዝን በረዶ ከሰማይ በሰዎች ላይ ወረደ፤ መቅሠፍቱ እጅግ አሠቃቂ ስለ ነበረ ሰዎች በበረዶው መቅሠፍት ምክንያት እግዚአብሔርን ተሳደቡ።


跟着我们:

广告


广告