Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 8:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 ይሁን እንጂ ንጉሡ አሁንም ልቡን በማደንደን የእስራኤልንም ሕዝብ አለቀቀም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 በዚህም ጊዜ እንኳ ፈርዖን ልቡን አደነደነ እንጂ፣ ሕዝቡን አልለቀቀም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ፈር​ዖ​ንም በዚህ ጊዜ ደግሞ ልቡን አደ​ነ​ደነ፤ ሕዝ​ቡ​ንም አል​ለ​ቀ​ቀም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ፈርዖንም በዚህ ጊዜ ደግሞ ልቡን አደነደነ፤ ሕዝቡንም አልለቀቀም።

参见章节 复制




ዘፀአት 8:32
11 交叉引用  

እንደገናም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ አሁን ወደ ግብጽ መመለስህ ስለ ሆነ፥ በሰጠሁህ ኀይል የምታደርጋቸውን ተአምራት በፈርዖን ፊት መፈጸም እንዳለብህ አትዘንጋ፤ ሆኖም እኔ የፈርዖንን ልብ ስለማደነድን ሕዝቡን በቀላሉ አይለቅም።


ንጉሡ ጓጒንቸሮቹ መሞታቸውን ባየ ጊዜ እግዚአብሔር እንዳለው ልቡን አደንድኖ አልሰማቸውም።


እግዚአብሔርም ሙሴ እንዳለው ሁሉ አደረገ፤ የዝንብ መንጋውም ከንጉሡና ከመኳንንቱ ከሕዝቡም ሁሉ ፊት አንድ ሳይቀር ተወገደ፤


ንጉሡም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “ጓጒንቸሮቹን ከእኔና ከሕዝቤ ዘንድ እንዲያርቅ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ ሕዝባችሁን እለቃለሁ” አላቸው።


ንጉሡ የሆነውን ሁሉ ለማጣራት ሰዎችን በላከ ጊዜ ከእስራኤላውያን እንስሶች አንድ እንኳ አለመሞቱን ተረዳ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ልቡን ስላደነደነ ሕዝቡን አለቀቀም።


አምላክ ሆይ! ለምን መንገድህን እንድንስት አደረግኸን? እንዳንፈራህስ ለምን ልባችንን አደነደንክ? ለአገልጋዮችህ፥ የአንተ ስለ ሆኑት ነገዶች ስትል እባክህ ተመለስ።


እንግዲህ አንተ ንስሓ ባለመግባትህና እልኸኛ በመሆንህ የእግዚአብሔር ቊጣና ትክክለኛ ፍርድ በሚገለጥበት ቀን ቅጣትህ እንዲበዛ ታደርጋለህ።


የግብጽ ንጉሥና ግብጻውያን እንዳደረጉት ስለምን ልባችሁን ታደነድናላችሁ? እስራኤላውያን የግብጽን ምድር ለቀው የወጡት፥ እግዚአብሔር ግብጻውያንን በብርቱ ከቀጣቸው በኋላ አልነበረምን?


跟着我们:

广告


广告