ዘፀአት 8:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 ሙሴ ግን እንዲህ አለ፦ “ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የምናቀርበው መሥዋዕት በግብጻውያን ዘንድ አጸያፊ ስለ ሆነ ይህን ማድረግ ተገቢ አይደለም፤ በግብጻውያን ዘንድ አጸያፊ የሆነውን መሥዋዕት በፊታቸው ብናቀርብ በድንጋይ አይወግሩንምን? 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም26 ሙሴ ግን እንዲህ አለ፤ “ይህ ትክክል አይሆንም፤ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የምናቀርበው መሥዋዕት በግብጻውያን ዘንድ አስጸያፊ ነው፤ ታዲያ በእነርሱ ዐይን አስጸያፊ የሆነውን መሥዋዕት ብናቀርብ አይወግሩንምን? 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 ሙሴም ከፈርዖን ዘንድ ወጣ፥ ወደ ጌታም ጸለየ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ሙሴም፥ “ለእግዚአብሔር ለአምላካችን ግብፃውያን እርም የሚሉትን እንሠዋለንና እንዲሁ ይሆን ዘንድ አይቻልም፤ እነሆ፥ ግብፃውያን እርም የሚሉትን እኛ በፊታቸው ብንሠዋ በድንጋይ ይወግሩናል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 ሙሴም፦ “ለእግዚአብሔር ለአምላካችን የግብፃውያንን ርኩሰት እንሰዋለንና እንዲህ ይደረግ ዘንድ አይገባም፤ እነሆ እኛ የግብፃውያንን ርኵሰት በፊታቸው ብንሠዋ አይወግሩንምን? 参见章节 |