Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 8:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እምቢ ብትል ግን በአንተ፥ በመኳንንትህና በሕዝብህ ቤቶች የዝንብ መንጋ እልካለሁ፤ የግብጻውያን ቤቶችና የቆሙበት ምድር በዝንብ መንጋ የተሞላ ይሆናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሕዝቤ እንዲሄዱ ባትለቅቃቸው፣ በአንተና በሹማምትህ ላይ፣ በሕዝብህና በቤቶችህ ላይ የዝንብ መንጋ እሰድዳለሁ። ያረፉበት መሬት እንኳ ሳይቀር፣ የግብጻውያን ቤቶች ሁሉ ዝንብ ብቻ ይሆናሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ፦ “ሂዱ፥ በምድሪቱ ውስጥ ለአምላካችሁ ሠዉ” አላቸው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሕዝ​ቤን ለመ​ል​ቀቅ እንቢ ብትል ግን እነሆ፥ በአ​ንተ፥ በሹ​ሞ​ች​ህም፥ በሕ​ዝ​ብ​ህም፥ በቤ​ቶ​ች​ህም ላይ የውሻ ዝንብ እሰ​ድ​ዳ​ለሁ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያን ቤቶች፥ የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም ምድር ሁሉ በውሻ ዝንብ ይመ​ላሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እንዲያገለግለኝ ሕዝቤን ልቀቅ። ሕዝቤንም ባትለቅቅ፥ እነሆ በአንተ፥ በባሪያዎችህም፥ በሕዝብህም፥ በቤቶችህም ላይ የዝንብ መንጎች እሰድዳለሁ፤ የግብፃውያን ቤቶች የሚኖሩባትም ምድር ሁሉ በዝንብ መንጎች ይሞላሉ።

参见章节 复制




ዘፀአት 8:21
7 交叉引用  

ተናካሽ ዝንቦችና ተናካሽ ትንኞች በአገሩ ሁሉ ላይ እንዲርመሰመሱ አዘዘ።


እነርሱን የሚያሠቃዩ ዝንቦችንና ጥፋትን የሚያስከትሉ እንቊራሪቶችን ወደ እነርሱ ላከ።


ቤተ መንግሥትህን፥ የመኳንንትህንና የሕዝብህን ቤቶች ሁሉ የአንበጣ መንጋ ይሞላዋል፤ ይህም ሁኔታ ከቀድሞ አባቶችህ ዘመን እስከ አሁን ከታየው መከራ ሁሉ የከፋ ይሆናል።’ ” ሙሴም ከፈርዖን ፊት ወጥቶ ሄደ።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “ነገ ጠዋት በማለዳ ወደ ንጉሡ ሄደህ ወደ ወንዝ ሲወርድ አግኘው፤ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ብለህ ንገረው፤ ‘ያገለግለኝ ዘንድ ሕዝቤን ልቀቅ፤


ነገር ግን በዚህ ምድር መካከል እኔ እግዚአብሔር መገኘቴን ታውቅ ዘንድ በዚያን ቀን ሕዝቤ የሚኖርባትን የጌሴምን ምድር ከዝንቦቹ መንጋ ነጻ አድርጌ እለያታለሁ።


እግዚአብሔርም የንጉሡ ቤተ መንግሥትና የመኳንንቱ ቤቶች ሁሉ በዝንብ መንጋ እንዲወረሩ አደረገ፤ መላዋም የግብጽ ምድር በዝንብ መንጋ ተበላሸች።


“ያም ዘመን በደረሰ ጊዜ ከዓባይ ወንዝ ዳርቻ ርቀት ግብጻውያን እንደ ዝንብ መንጋ፥ አሦራውያንም ከአገራቸው እንደ ንብ ሠራዊት እየተመሙ ይመጡ ዘንድ እግዚአብሔር ምልክት ይሰጣቸዋል።


跟着我们:

广告


广告