Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 8:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ከዚህ በኋላ ሙሴና አሮን ከንጉሡ ፊት ወጥተው ሄዱ፤ በንጉሡ ላይ ያመጣቸውንም ጓጒንቸሮች ያስወግድለት ዘንድ ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ሙሴና አሮን ከፈርዖን ዘንድ ከተመለሱ በኋላ፣ በፈርዖን ላይ ስላመጣቸው ጓጕንቸሮች ሙሴ ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጌታም ሙሴን አለው፦ “አሮንን ‘በትርህን ዘርጋ፥ በግብጽ ምድር ሁሉ ተናካሽ ትንኝ እንዲሆን የምድሩን ትቢያ ምታ በለው።’”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ሙሴና አሮ​ንም ከፈ​ር​ዖን ዘንድ ወጡ፤ ሙሴም ፈር​ዖን እንደ ቀጠ​ረው ሰለ ጓጕ​ን​ቸ​ሮቹ መራቅ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ሙሴና አሮንም ከፈርዖን ዘንድ ወጡ። ሙሴም በፈርዖን ላይ ስላመጣቸው ጓጕንቸሮች ወደ እግዚአብሔር ጮኸ።

参见章节 复制




ዘፀአት 8:12
10 交叉引用  

ተናካሽ ዝንቦችና ተናካሽ ትንኞች በአገሩ ሁሉ ላይ እንዲርመሰመሱ አዘዘ።


ሙሴም ከንጉሡ ፊት ወጥቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።


ሙሴ ግን እግዚአብሔር አምላኩን በመማለድ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር ሆይ፥ በሥልጣንህና በታላቅ ኀይልህ ከግብጽ ምድር ያወጣኸውን ሕዝብህን እስከዚህ የምትቈጣው ስለምነው?


ሙሴ በጸለየውም መሠረት እግዚአብሔር በየቤቱ፥ በየቅጽር ግቢውና በየመስኩ ያሉት ጓጒንቸሮች ሁሉ ሞቱ።


ሙሴም ከንጉሡ ፊት ወጥቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤


ንጉሡም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “ጓጒንቸሮቹን ከእኔና ከሕዝቤ ዘንድ እንዲያርቅ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ፤ ለእግዚአብሔር መሥዋዕት ያቀርቡ ዘንድ ሕዝባችሁን እለቃለሁ” አላቸው።


ሙሴ ከንጉሡ ፊት በመውጣት ከከተማው ውጪ ሄደ፤ እጁንም ዘርግቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ ነጐድጓዱና በረዶው ዝናቡም በአንድ ጊዜ ቆመ።


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እስራኤላውያን ደግመው አንድ ጊዜ ይህን እንዲለምኑኝ አደርጋለሁ፤ ቊጥራቸውንም እንደ በጎች መንጋ አበዛዋለሁ።


መልካሙንና ቅኑን ነገር አስተምራችኋለሁ እንጂ ስለ እናንተ መጸለይን በመተው እግዚአብሔርን እበድል ዘንድ ይህ ከእኔ ይራቅ።


跟着我们:

广告


广告