Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 7:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ አሮንም በንጉሡና በመኳንንቱ ፊት በትሩን አንሥቶ የወንዙን ውሃ መታው። የወንዙም ውሃ ተለውጦ ደም ሆነ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ሙሴና አሮን እግዚአብሔር እንደ አዘዛቸው አደረጉ። እርሱም በፈርዖንና በሹማምቱ ፊት በትሩን አንሥቶ የአባይን ወንዝ ውሃ መታ፤ ውሃውም በሙሉ ወደ ደም ተለወጠ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ሙሴና አሮንም ልክ ጌታ እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ በትሩንም አነሣ፥ በፈርዖንና በአገልጋዮቹም ፊት በዓባይ ወንዝ የነበረውን ውኃ መታ፤ በዓባይ ወንዝ ላይ የነበረው ውኃ ሁሉ ወደ ደም ተቀየረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሙሴና አሮ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው እን​ዲሁ አደ​ረጉ፤ አሮ​ንም በት​ሩን አነሣ፤ በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት የወ​ን​ዙን ውኃ መታ፤ የወ​ን​ዙም ውኃ ሁሉ ተለ​ውጦ ደም ሆነ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፤ በትሩንም አነሣ፤ በፈርዖንና በባሪያዎቹም ፊት የወንዙን ውኃ መታ፤ የወንዙም ውኃ ሁሉ ተለውጦ ደም ሆነ።

参见章节 复制




ዘፀአት 7:20
14 交叉引用  

ኤልሳዕም ወደ ግያዝ መለስ ብሎ “በፍጥነት ተነሥና የእኔን ምርኲዝ ይዘህ ሂድ! ለአንድም ሰው ሰላምታ ለመስጠት እንኳ በመንገድ አትቁም፤ ማንም ሰው ሰላምታ ቢሰጥህ አጸፋውን ለመመለስ ጊዜ አታጥፋ፤ በቀጥታ ወደ ቤት ሄደህ የእኔን ምርኲዝ በልጁ ፊት ላይ አኑር!” አለው።


የወንዞቻቸውንም ውሃ ወደ ደም ለወጠ፤ ዓሣዎቻቸውንም ሁሉ ገደለ።


የወንዞቻቸውን ውሃ ወደ ደም ለወጠ፤ ስለዚህ ግብጻውያን ከወንዞቻቸው ውሃ መጠጣት አልቻሉም።


እነዚህን ሁለት ተአምራት አይተው ባያምኑና ቃልህንም ባይሰሙ፥ ከዐባይ ወንዝ ጥቂት ውሃ ወስደህ በመሬት ላይ አፍስሰው፤ ከአባይ ወንዝ የወሰድከውም ውሃ በደረቀ ምድር ላይ ወደ ደም ይለወጣል።”


ስለዚህ ሙሴና አሮን ወደ ፈርዖን ሄደው እግዚአብሔር እንዳዘዛቸው አደረጉ፤ አሮንም በትሩን በንጉሡና በመኳንንቱ ፊት በጣለው ጊዜ ተለውጦ እባብ ሆነ።


በወንዝ ውስጥ ያሉት ዓሣዎች ሁሉ ሞቱ፤ የዐባይ ወንዝ ውሃ ስለ ገማ ግብጻውያን ሊጠጡት አልቻሉም። በግብጽ ምድር ደም የሌለበት ስፍራ አልነበረም።


ሙሴና አሮንም እግዚአብሔር ያዘዛቸውን ሁሉ ፈጸሙ።


እግዚአብሔር ሆይ! ፈረሶችህንና ሠረገላዎችህን ወደ ድል በመራኸቸው ጊዜ፥ ኀይለኛው ቊጣህ በወንዞች ላይ ነበርን? ወይስ በባሕሩ ላይ ተቈጥተህ ነበርን?


ሁለተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ ትልቅ ተራራ የሚመስል ነገር እየነደደ ወደ ባሕር ተጣለ፤ የባሕር ሢሶው ደም ሆነ፤


跟着我们:

广告


广告