ዘፀአት 39:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 የደረቱንም ኪስ ኤፉዱ ከተሠራባቸው ተመሳሳይ ነገሮች በተመሳሳይ የጥበብ ጥልፍ ሠሩት፤ 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 የደረት ኪሱንም ጥበበኛ ባለሙያ እንደሚሠራው ሥራ በተመሳሳይ መንገድ ሠሩት፤ እንደ ኤፉዱም ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ በቀጭኑም ከተፈተለ በፍታ ሠሩት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 የደረቱን ኪስ ብልህ ሠራተኛ እንደሠራው እንደ ኤፉዱ አሠራር ከወርቅ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ግምጃና ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ሠራው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ልብሰ እንግድዓውን ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ፥ እንደ ልብሰ መትከፉ አሠራር ከወርቅና ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ፥ ከተፈትለም ከጥሩ በፍታ አደረጉ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው፥ የደረቱን ኪስ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ እንደ ኤፉዱ አሠራር ከወርቅና ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ አደረገው። 参见章节 |