Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 39:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 መታጠቂያውንም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ ጥሩ በፍታ ሠርተው እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በጥልፍ ጥበብ አስጌጡት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 መታጠቂያው እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታና ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊና ከቀይ ማግ፣ የጥልፍ ጠላፊ ሥራ ሆኖ የተሠራ ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ የተጠለፈ መታጠቂያ ሠሩ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ከተ​ፈ​ተ​ለም ከጥሩ በፍታ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊም፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ በጥ​ልፍ አሠ​ራር የተ​ሠራ መታ​ጠ​ቂ​ያ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው አደ​ረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊም ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ በጥልፍ አሠራር የተሠራ መታጠቂያውን አደረጉ።

参见章节 复制




ዘፀአት 39:29
6 交叉引用  

ሰማያዊና ሐምራዊ፥ ቀይም ከፈይ፥ ጥሩ በፍታ፥ ከፍየል ጠጒር የተሠራ ልብስ፥


“ለድንኳኑም ደጃፍ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ በጥልፍ ያጌጠ መጋረጃ አድርግለት።


ለአደባባዩ በር ርዝመታቸው ዘጠኝ ሜትር የሆነ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ የተሠራ በጥልፍ ያጌጠ መጋረጃ ይኑረው፤ የሚደግፉትም አራት እግሮች ያሉአቸው አራት ምሰሶዎች ይኑሩት።


“የአሮንን ሸሚዝና መጠምጠሚያ ከጥሩ በፍታ ሥራው፤ መታጠቂያውም ከጥሩ በፍታ ተሠርቶ በጥልፍ ጥበብ ያጌጠ ይሁን።


የራስ መጠምጠሚያዎችን፥ ቆቦችንና ሱሪዎችን፥


የተቀደሰውንም የአክሊል ምልክት ከንጹሕ ወርቅ ሠርተው “ለእግዚአብሔር አገልግሎት የተለየ” የሚል ቃል እንደ ማኅተም ቀረጹበት።


跟着我们:

广告


广告