ዘፀአት 38:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም27 ከብሩም ሦስት ሺህ አራት መቶ ኪሎ የሚሆነው ለተቀደሰው ድንኳንና ለመጋረጃዎች መቆሚያ የሚሆኑ አንድ መቶ እግሮች የተሠሩበት ነበር፤ ይኸውም ለእያንዳንዱ እግር ሠላሳ አራት ኪሎ ግራም ተመድቦለት ነው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም27 አንድ መቶ የብር መክሊቶች የመቅደሱንና የመጋረጃዎቹን መቆሚያዎች ለመሥራት አገልግሎት ላይ ውለው ነበር፤ ይኸውም ከአንድ መቶ መክሊቶች አንድ መቶ መቆሚያዎች ሲሆን፣ ለእያንዳንዱ መቆሚያ አንድ መክሊት ማለት ነው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)27 መቶው የብር መክሊት የመቅደሱንና የመጋረጃውን እግሮች ለመሥራት ነበረ፤ ከመቶ መክሊት መቶ እግሮች ተሠሩ ይኸውም ለአንድ እግር አንድ መክሊት ማለት ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)27 መቶውም የብር መክሊት ለድንኳኑ ምሰሶዎች እግሮችና ለመጋረጃው ምሰሶዎች እግሮች ተደረገ፤ መቶውም መክሊት ለመቶ እግሮች፤ ለአንድ እግርም አንድ መክሊት ሆነ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)27 መቶውም የብር መክሊት የመቅደሱንና የመጋረጃውን እግሮች ለመሥራት ነበረ፤ ከመቶውም መክሊት መቶ እግሮች አደረገ፤ ለአንድ እግርም አንድ መክሊት ነበረ። 参见章节 |