Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 36:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 መጋረጃዎችንም ከጥሩ በፍታ ሠሩ፤ እርሱም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ የተፈተለ ሲሆን የኪሩቤል ሥዕል ተጠልፎበት ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ፣ እጀ ጥበብ ባለሙያም ኪሩቤል የተጠለፉበት መጋረጃ ሠራ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 መጋረጃውንም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይም ግምጃና ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ ሠራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሠራው ኪሩቤልን በእርሱ ላይ አደረገ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 መጋ​ረ​ጃ​ው​ንም ከሰ​ማ​ያ​ዊና ከሐ​ም​ራዊ፥ ከቀ​ይም ግምጃ፥ ከተ​ፈ​ተ​ለም ከጥሩ በፍታ አደ​ረጉ፤ ኪሩ​ቤ​ል​ንም በጥ​ልፍ ሥራ በእ​ርሱ ላይ አደ​ረጉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 መጋረጃውንም ከሰማያዊና ከሐምራዊ ከቀይም ግምጃ፥ ከተፈተለም ከጥሩ በፍታ አደረጉ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤልን በእርሱ ላይ አደረጉ።

参见章节 复制




ዘፀአት 36:35
8 交叉引用  

“እንዲሁም የተቀደሰውን ድንኳን ውስጠኛ ክፍል ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ በፍታ በተሠሩ ዐሥር መጋረጃዎች አብጀው፤ በእነርሱም ላይ ኪሩቤል በጥልፍ ጥበብ እንዲሳሉ አድርግ።


ይህንንም መሠዊያ ከቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ከተሰቀለው መጋረጃ ውጪ አኑረው፤ እኔም በዚያ ለአንተ እገለጥልሃለሁ፤


ተራዳዎቹንም በወርቅ ለበጡአቸው፤ ዋልታዎቻቸውንም የመወርወሪያው መተላለፊያ ይሆኑ ዘንድ ከወርቅ ሠሩ፤ መወርወሪያዎቹም በወርቅ የተለበጡ ነበሩ።


መጋረጃዎቹን የሚያያይዙ አራት ምሰሶዎችንም ከግራር እንጨት ሠርተው በወርቅ ለበጡአቸው፤ ኩላቦቻቸውንም ከወርቅ ሠሩ፤ ምሰሶዎቹ የሚቆሙባቸውን አራት እግሮችንም ከብር ሠሩ፤


ታቦቱንም ወደ ድንኳኑ ውስጥ አስገባውና የሚከለልበትን መጋረጃ ሰቀለ፤ በዚህም ዐይነት ልክ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ታቦቱን ሸፈነው።


በዚያን ጊዜ የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀዶ ከሁለት ተከፈለ፤ ምድርም ተናወጠች፤ አለቶችም ተሰነጠቁ፤


የምንገባውም በመጋረጃው፥ ማለትም በሥጋው አማካይነት በከፈተልን በአዲሱና ሕያው በሆነው መንገድ ነው።


跟着我们:

广告


广告