ዘፀአት 35:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም35 በአንጥረኛ፥ በፕላን አውጪ ባለሞያ፥ ጥሩ በፍታ፥ ሰማያዊ፥ ሐምራዊና ቀይ ቀለም የተነከረ ከፈይ ሌላውንም የልብስ ሥራ በሚያከናውኑ ሸማኔዎች የተሠራውን ነገር ሁሉ ለማስጌጥ የሚችሉበትን ብልኀት ሰጥቶአቸዋል፤ እነርሱ ማናቸውንም የጥበብ ሥራ ለመሥራትና በብልኀት የሚሠራውንም ሁሉ ዕቅድ ለማውጣት የሚችሉ ናቸው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም35 የእጅ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ዕቅድ አውጭዎች፣ በሰማያዊ በሐምራዊና በቀይ ማግ፣ በቀጭን ሐር ጥልፍ ጠላፊዎችና ፈታዮች፤ ሁሉም ዋና የእጅ ጥበብ ባለሙያዎችና ዕቅድ አውጭዎች በመሆን ማንኛውንም ዐይነት ሥራ ያከናውኑ ዘንድ በጥበብ ሞልቷቸዋል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)35 በአንጥረኝነት፥ በንድፍ፥ በሰማያዊ፥ በሐምራዊ፥ በቀይ ግምጃና በጥሩ በፍታ በመጥለፍ፥ ሸማኔ በሚሠራው ሥራ፥ በማናቸውንም ሥራና በብልሃት የሚሠራውን ሁሉ እንዲያደርጉ በእነርሱ ልብ ጥበብን ሞላ።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)35 በአንጥረኛ፥ በብልህ ሠራተኛም፥ በሰማያዊና በሐምራዊ፥ በቀይም ግምጃ፥ በጥሩ በፍታም በሚሠራ ጠላፊ፥ በሸማኔም ሥራ የሚሠራውን፥ ማናቸውንም ሥራና በብልሃት የሚሠራውን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በእነርሱ ልብ ጥበብን ሞላ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)35 በአንጥረኛ፥ በብልህ ሠራተኛም፥ በሰማያዊና በሐምራዊ በቀይም ግምጃ በጥሩ በፍታም በሚሠራ ጠላፊ፥ በሸማኔም ሥራ የሚሠራውን፥ ማናቸውንም ሥራና በብልሃት የሚሠራውን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በእነርሱ ልብ ጥበብን ሞላ። 参见章节 |
የሑራም አቢ እናት ከዳን ነገድ ስትሆን፥ አባቱም የጢሮስ ተወላጅ ነው፤ ሑራም አቢ ከወርቅ፥ ከብር፥ ከነሐስ፥ ከብረት፥ ከድንጋይና ከእንጨት ልዩ ልዩ ነገሮችን የመሥራት ችሎታ አለው፤ እንዲሁም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ጨርቅና ከበፍታ የተለያየ ልብስ መሥራት ይችላል፤ ከዚህም ሌላ ልዩ ልዩ ቅርጽ ማውጣትና በተሰጠውም ንድፍ መሠረት ሁሉን ነገር መሥራት ይችላል፤ ስለዚህ ይህን ሰው በእጅ ሥራ ከሠለጠኑ ከአንተ ሰዎችና ከእነዚያ ለአባትህ ይሠሩ ከነበሩ ሰዎች ጋር እንዲሠራ አድርገው።