ዘፀአት 35:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 እግዚአብሔር እርሱን በመንፈሱ ኀይል እንዲሞላ አድርጎ ማናቸውንም የጥበብ ሥራ መሥራት እንዲችል ብልኀትን፥ ችሎታንና ማስተዋልን ሰጥቶታል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም31 በጥበብ፣ በችሎታና በዕውቀት፣ በማንኛውም ዐይነት ሙያ የእግዚአብሔርን መንፈስ ሞልቶበታል፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 በእግዚአብሔር መንፈስ፥ በጥበብ፥ በማስተዋል፥ በእውቀት በሥራ ሁሉ ብልሃት ሞላው፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 በሥራ ሁሉ ብልሃት፥ በጥበብም፥ በማስተዋልም፥ በዕውቀትም የእግዚአብሔርን መንፈስ ሞላበት፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 በሥራ ሁሉ ብልሃት በጥበብም በማስተዋልም በእውቀትም የእግዚአብሔርን መንፈስ ሞላበት፤ 参见章节 |
የሑራም አቢ እናት ከዳን ነገድ ስትሆን፥ አባቱም የጢሮስ ተወላጅ ነው፤ ሑራም አቢ ከወርቅ፥ ከብር፥ ከነሐስ፥ ከብረት፥ ከድንጋይና ከእንጨት ልዩ ልዩ ነገሮችን የመሥራት ችሎታ አለው፤ እንዲሁም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ፥ ከቀይ ጨርቅና ከበፍታ የተለያየ ልብስ መሥራት ይችላል፤ ከዚህም ሌላ ልዩ ልዩ ቅርጽ ማውጣትና በተሰጠውም ንድፍ መሠረት ሁሉን ነገር መሥራት ይችላል፤ ስለዚህ ይህን ሰው በእጅ ሥራ ከሠለጠኑ ከአንተ ሰዎችና ከእነዚያ ለአባትህ ይሠሩ ከነበሩ ሰዎች ጋር እንዲሠራ አድርገው።