Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 34:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እግዚአብሔር ሙሴን፦ “ከአንተም ሆነ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ቃል ኪዳን የምገባው በዚህ ቃል መሠረት ስለ ሆነ ይህን ቃል በመጽሐፍ ጻፈው” አለው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ከዚያም እግዚአብሔር ሙሴን፣ “እነዚህን ቃሎች ጻፋቸው፤ በእነዚህ ቃሎች መሠረት ከአንተና ከእስራኤል ጋራ ቃል ኪዳን አድርጌአለሁና” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ጌታም ሙሴን፦ “በእነዚህ ቃሎች መጠን ከአንተና ከእስራኤል ጋር ቃል ኪዳን አድርጌአለሁና እነዚህን ቃሎች ጻፍ” አለው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በእ​ነ​ዚህ ቃሎች ከአ​ን​ተና ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ቃል ኪዳን አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና እነ​ዚ​ህን ቃሎች ጻፍ” አለው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 እግዚአብሔርም ሙሴን፦ በእነዚህ ቃሎች መጠን ከአንተና ከእስራኤል ጋር ቃል ኪዳን አድርጌአለሁና እነዚህን ቃሎች ጻፍ አለው።

参见章节 复制




ዘፀአት 34:27
6 交叉引用  

ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን “ዘወትር ሲታወስ እንዲኖር የዚህን ድል ታሪክ ጻፈው፤ ለኢያሱም ዐማሌቃውያንን ከምድር ጨርሼ የማጠፋቸው መሆኔን ንገረው” አለው።


ሙሴም የእግዚአብሔርን ትእዛዞች ሁሉ ጻፈ፤ በማግስቱም ጠዋት በማለዳ በተራራው ሥር መሠዊያ ሠራ፤ ለእያንዳንዱም የእስራኤል ነገድ አንድ የድንጋይ ዐምድ አኖረ፤


ከዚህ በኋላ የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ወስዶ ድምፁን ከፍ በማድረግ ለሕዝቡ አነበበ፤ ሕዝቡም “ለእግዚአብሔር እንታዘዛለን እርሱ ያዘዘውንም ሁሉ እንፈጽማለን” አሉ።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከዚህ በፊት በምድር ላይ በማንኛውም ሕዝብ ዘንድ ሆኖ የማያውቅ ድንቅ ነገር በሕዝብህ ፊት አደርጋለሁ፤ አስፈሪ የሆነ ድንቅ ነገር ስለማደርግ እኔ እግዚአብሔር የማደርጋቸውን ድንቅ ነገሮች በመካከላቸው የምትኖርባቸው ሕዝቦች ሁሉ ያያሉ።


ከዚያ በኋላ ሙሴ የእግዚአብሔርን ሕግ ጽፎ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ታቦት አገልጋዮች ለሆኑት ለሌዋውያን ካህናትና ለእስራኤል ሕዝብ አለቆች ሰጣቸው።


ቃል ኪዳኑን ገልጾላችሁ እንድትጠብቁት አዘዛችሁ እርሱም በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ የጻፈው ዐሥሩ ትእዛዝ ነው።


跟着我们:

广告


广告