Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 34:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 “ብረት አቅልጣችሁ አማልክት አትሥሩ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 “ቀልጠው የሚሠሩ አማልክትን አታብጅ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ቀልጠው የተሠሩ የአማልክት ምስሎች ለአንተ አታድርግ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ቀል​ጠው የተ​ሠ​ሩ​ትን አማ​ል​ክት ለአ​ንተ አታ​ድ​ርግ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ቀልጠው የተሠሩትን የአማልክት ምስሎች ለአንተ አታድርግ።

参见章节 复制




ዘፀአት 34:17
14 交叉引用  

ይልቁንም ከአንተ በፊት መሪዎች ከነበሩ ሰዎች የከፋ ኃጢአት ሠራህ፤ እኔንም ትተህ ጣዖቶችና ከብረት የተቀረጹ ምስሎችን ለማምለክ በመሥራትህ ቊጣዬን አነሣሥተሃል፤


የእስራኤልን ነገሥታት መጥፎ አርአያነት ተከተለ፤ ባዓል ተብሎ የሚጠራ የጣዖት ምስሎችን አቅልጦ ሠራ፤


እኔን ብቻ አምልኩ እንጂ፥ ከብርና ከወርቅ ጣዖቶች ሠርታችሁ አታምልኩ፤


“በሰማይም ሆነ በምድር ወይም ከምድር በታች ባለው ውሃ ውስጥ ከሚኖሩት ነገሮች የማንኛውንም ዐይነት ምስል ጣዖት አድርገህ አትሥራ፤


“እኔን የምታከብሩባቸው በዓመት ሦስት በዓላት ይኑሩአችሁ፤


እነርሱ እንዲከተሉት ካዘዝኳቸው መንገድ ወዲያውኑ ወጥተዋል፤ ከቀለጠ ወርቅ ጥጃ ሠርተውም ሰግደውለታል፤ መሥዋዕትም አቅርበውለት ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን አምላካችን ይህ ነው’ ብለዋል።


ሁሉም ሞኞችና አላዋቂዎች ሆኑ፤ የሠሩአቸው ምስሎች ሐሰተኞች ስለ ሆኑና ሕይወትም ስለሌላቸው አንጥረኛው በሠራቸው ጣዖቶች አፍሮባቸዋል።


“ወደ ጣዖት አምልኮ አትመለሱ፤ ወይም ብረት አቅልጣችሁ አማልክትን አትሥሩ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ።


እንግዲህ እኛ የእርሱ ልጆች ከሆንን ‘እግዚአብሔር በሰው ጥበብና አሳብ ከወርቅ ወይም ከብር ወይም ከድንጋይ የተሠራውን ቅርጽ ይመስላል’ ብለን ማሰብ አይገባንም።


ይህ ጳውሎስ ‘በሰው እጅ የተሠሩ ምስሎች አማልክት አይደሉም’ እያለ በኤፌሶን ብቻ ሳይሆን ከጥቂት አገሮች በቀር በመላዋ እስያ ምን ያኽል ብዙ ሕዝብ እንዳግባባና እንዳሳመነ እናንተ ራሳችሁ ያያችሁትና የሰማችሁት ነው።


“ ‘እንጨት ጠርቦ፥ ድንጋይ አለዝቦ፥ ብረት አቅልጦ ጣዖት በመሥራት በስውር የሚሰግድለት ማንኛውም ሰው የተረገመ ይሁን! እግዚአብሔር የጣዖት አምልኮን ይጠላል።’ “ሕዝቡም ሁሉ ሲመልሱ ‘አሜን!’ ይበሉ።


“ ‘በሰማይ፥ ወይም በምድር፥ ወይም ከምድር በታች በውሃ ውስጥ ከሚገኙት ነገሮች የተቀረጹ ምስሎች ሠርተህ አታምልካቸው፤


ልጁም ገንዘቡን መልሶ ለእናቱ ሰጣት፤ እርስዋም “እኔ ራሴ ብሩን ለእግዚአብሔር ስለ ልጄ የተለየ አደርገዋለሁ፤ ከእንጨት ተሠርቶ በብር የተለበጠ ጣዖት ማሠሪያም ይሆናል፤ ስለዚህ ብሩን ለአንተ መልሼ እሰጥሃለሁ” አለችው።


跟着我们:

广告


广告