Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 34:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የመጀመሪያዎቹን የሚመስሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ቅረጽ፤ እኔም አንተ በሰበርካቸው ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት እጽፍባቸዋለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ሙሴን አለው፤ “እንደ መጀመሪያዎቹ ያሉ ሁለት የድንጋይ ጽላት ጥረብ፤ እኔም አንተ በሰበርሃቸው በመጀመሪያዎቹ ጽላት ላይ የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደ ፊተኞቹ አድርገህ ጥረብ፥ በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን አለው፥ “ሁለት የድ​ን​ጋይ ጽላት እንደ ፊተ​ኞቹ አድ​ር​ገህ ቅረጽ፤ ወደ እኔም ወደ ተራራ ውጣ፤ በሰ​በ​ር​ሃ​ቸው በፊ​ተ​ኞቹ ጽላት የነ​በ​ሩ​ትን ቃላት እጽ​ፍ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች እንደ ፊተኞች አድርገህ ጥረብ፤ በሰበርኻቸው በፊተኞቹ ጽላቶች የነበሩትን ቃሎች እጽፍባቸዋለሁ።

参见章节 复制




ዘፀአት 34:1
11 交叉引用  

እግዚአብሔር ሆይ! ቃልህ ዘለዓለማዊ ነው፤ በሰማይም ጸንቶ ይኖራል።


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እኔ ወዳለሁበት ወደ ተራራው ወጥተህ በዚያ ቈይ፤ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችንም እሰጥሃለሁ፤ በእነርሱም ላይ ለሕዝቡ መመሪያዎች ይሆኑ ዘንድ እኔ የጻፍኳቸው ትእዛዞችና ኅጎች ይገኛሉ።”


እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ማነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት በድንጋይ ላይ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች ሰጠው።


እነዚህም ጽላቶች የእግዚአብሔር ሥራ ናቸው። በላያቸው ላይ ያሉት ጽሑፎች የተቀረጹት በእግዚአብሔር ነው።


ሙሴም ወደ ሰፈሩ ተጠግቶ ጥጃውንና ጭፈራ ባየ ጊዜ እጅግ ተቈጣ፤ ይዞአቸው የመጣውንም ጽላቶች በተራራው ሥር ወርውሮ ሰባበራቸው።


ሙሴም ምንም ሳይበላና ሳይጠጣ ከእግዚአብሔር ጋር አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቈየ፤ ጌታም በጽላቶቹ ላይ የቃል ኪዳን ቃላት የሆኑትን ዐሥሩን ትእዛዞች ጻፈ።


ስለዚህ ሙሴ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ልክ እንደ ፊተኞቹ ቀረጸ፤ በማግስቱም ጠዋት በማለዳ ተነሥቶ ልክ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ጽላቶቹን ይዞ ወደ ሲና ተራራ ወጣ።


ስለዚህ ሌላ የብራና ጥቅል ወስጄ ለጸሐፊዬ ለባሮክ ሰጠሁት፤ እርሱም በቃል የነገርኩትን ሁሉ ጻፈበት፤ በዚህ ዐይነት የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም ባቃጠለው ብራና ተጽፎ የነበረውን ጻፈ፤ ሌሎችም ብዙ ተመሳሳይ ቃሎች ተጨምረውበታል።


ቃል ኪዳኑን ገልጾላችሁ እንድትጠብቁት አዘዛችሁ እርሱም በሁለት የድንጋይ ጽላቶች ላይ የጻፈው ዐሥሩ ትእዛዝ ነው።


跟着我们:

广告


广告