ዘፀአት 32:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 እነርሱ እንዲከተሉት ካዘዝኳቸው መንገድ ወዲያውኑ ወጥተዋል፤ ከቀለጠ ወርቅ ጥጃ ሠርተውም ሰግደውለታል፤ መሥዋዕትም አቅርበውለት ‘ከግብጽ ምድር ያወጣን አምላካችን ይህ ነው’ ብለዋል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም8 “ካዘዝኋቸው ፈቀቅ ለማለት ፈጣኖች ሆኑ፤ ለራሳቸውም በጥጃ ምስል የተቀረጸ ጣዖትን ሠሩ፤ ለርሱም ሰገዱለት፤ ሠዉለትም፤ እንዲሁም፣ ‘እስራኤል ሆይ፤ ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ እነዚህ ናቸው’ አሉ።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ካዘዝኋቸው መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ፤ ለራሳቸውም ቀልጦ የተሠራ ጥጃ ሠሩ፥ ሰገዱለት፥ ሠዉለትም፦ ‘እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብጽ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው’ አሉ።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ካዘዝኋቸው መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ፤ ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ለራሳቸው አደረጉ፤ ሰገዱለትም፤ ሠዉለትም፤ 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ካዘዝኋቸው መንገድ ፈጥነው ፈቀቅ አሉ፤ ቀልጦ የተሠራ የጥጃ ምስል ለራሳቸው አደረጉ፥ ሰገዱለትም፥ ሠውለትም፦ እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አሉ ሲል ተናገረው። 参见章节 |