Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 32:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ስለዚህ በሰፈሩ ደጃፍ ቆሞ “የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ!” በማለት ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ፤ ሌዋውያንም ሁሉ በዙሪያው ተሰበሰቡ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ስለዚህ በሰፈሩ መግቢያ ላይ ቆሞ፣ “የእግዚአብሔር የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ” አለ፤ ሌዋውያኑም ሁሉ ከርሱ ጋራ ሆኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሙሴ በሰፈሩ ደጅ ቆሞ፦ “የጌታ ወገን የሆነ ሁሉ ወደ እኔ ይምጣ!” አለ፤ የሌዊ ልጆች ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሙሴ በሰ​ፈሩ ደጅ ቆሞ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወገን የሆነ ወደ እኔ ይምጣ” አለ፤ የሌዊ ልጆች ሁሉ ወደ እርሱ ተሰ​በ​ሰቡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 በሰፈሩ ደጅ ቆሞ፦ የእግዚአብሔር ወገን የሆነ ወደ እኔ ይምጣ! አለ፤ የሌዊም ልጆች ሁሉ ወደ እርሱ ተሰበሰቡ።

参见章节 复制




ዘፀአት 32:26
8 交叉引用  

ከኢዮአብ ወታደሮች አንዱ በዐማሳ ሬሳ አጠገብ ቆሞ “ኢዮአብንና ዳዊትን የምትከተሉ ሁሉ ኢዮአብን ተከተሉ!” ሲል ድምፁን ከፍ አድርጎ ተናገረ።


ኢዩ ቀና ብሎ ወደ ላይ በመመልከት ድምፁን ከፍ አድርጎ “ከእኔ ጋር የሚተባበር ማን ነው?” ሲል ጮኸ፤ ቊጥራቸው ከሁለት እስከ ሦስት የሆነ የቤተ መንግሥት ባለ ሥልጣኖች በመስኮት ብቅ ብለው ወደ እርሱ ተመለከቱ፤


ዐመፀኞችን ለመቃወም ከጐኔ የሚቆም ማነው? ከክፉ አድራጊዎችስ ጋር ስለ እኔ የሚከራከር ማን ነው?


አሮን ሕዝቡን በጠላቶቻቸው ፊት መሳለቂያ እስኪሆኑ ድረስ መረን እንደ ለቀቃቸው ሙሴ ተመለከተ።


እንዲህም አላቸው፦ “እያንዳንዳችሁ ሰይፋችሁን መዛችሁ ከዚህ በር እስከ ወዲያኛው በር ድረስ በሰፈሩ ውስጥ በመመላለስ ያለ ምንም ምሕረት ወንድሞቻችሁን፥ ወዳጆቻችሁንና ጐረቤቶቻችሁን እንድትገድሉ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር አዞአችኋል።”


ከእኔ ጋር ያልሆነ ሁሉ ተቃዋሚዬ ነው፤ ከእኔም ጋር የማይሰበስብ ይበትናል።


እነርሱ ለአንተ ሲሉ ወላጆቻቸውን ረስተዋል፤ ከዘመዶቻቸው ተለይተዋል፤ ልጆቻቸውን ትተዋል፤ ቃልህን አክብረዋል። ቃል ኪዳንህንም ጠብቀዋል፤


ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ሰይፍ የያዘ አንድ ጐልማሳ በድንገት በፊቱ ቆሞ ታየው፤ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀረብ ብሎ “አንተ የእኛ ወገን ነህ ወይስ የጠላቶቻችን?” አለው።


跟着我们:

广告


广告