Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 32:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 እነዚህም ጽላቶች የእግዚአብሔር ሥራ ናቸው። በላያቸው ላይ ያሉት ጽሑፎች የተቀረጹት በእግዚአብሔር ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ጽላቱ የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ፤ በጽላቱ ላይ የተቀረጸ ጽሕፈትም የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበር።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጽላቶቹ የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ፥ በጽላቶቹ ላይ የተቀረው ጽሑፍም የእግዚአብሔር ጽሑፍ ነበረ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ጽላቱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ነበሩ፤ ጽሕ​ፈ​ቱም በጽ​ላቱ ላይ የተ​ቀ​ረ​ጸ​ባ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽሕ​ፈት ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ጽላቶቹም የእግዚአብሔር ሥራ ነበሩ፤ ጽሕፈቱም በጽላቶች ላይ የተቀረጸባቸው የእግዚአብሔር ጽሕፈት ነበረ።

参见章节 复制




ዘፀአት 32:16
12 交叉引用  

ምነው በብረት መሣሪያና በእርሳስ ተጽፈው ወይም በድንጋይ ላይ ተቀርጸው ለዘለዓለም እንዲኖሩ ቢደረግ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር!


እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ማነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት በድንጋይ ላይ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች ሰጠው።


ከዚህ በኋላ ሙሴ ተነሥቶ በሁለቱም በኩል ዐሥሩ ትእዛዞች የተጻፉባቸውን ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች በመያዝ ከተራራው ወረደ።


ኢያሱ የሕዝቡን ጫጫታ ሰምቶ ሙሴን “በሰፈሩ ውስጥ የጦርነት ድምፅ ይሰማል” አለው።


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የመጀመሪያዎቹን የሚመስሉ ሁለት የድንጋይ ጽላቶች ቅረጽ፤ እኔም አንተ በሰበርካቸው ጽላቶች ላይ የነበሩትን ቃላት እጽፍባቸዋለሁ።


ስለዚህ ሙሴ ሁለት የድንጋይ ጽላቶችን ልክ እንደ ፊተኞቹ ቀረጸ፤ በማግስቱም ጠዋት በማለዳ ተነሥቶ ልክ እግዚአብሔር እንዳዘዘው ጽላቶቹን ይዞ ወደ ሲና ተራራ ወጣ።


እናንተስ በእኛ አገልግሎት የመጣችሁ የክርስቶስ መልእክት መሆናችሁ ግልጥ ነው፤ ይህም መልእክት የተጻፈው በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በቀለም አይደለም፤ እንዲሁም በሰው ልብ ጽላት ላይ እንጂ በድንጋይ ጽላት ላይ የተጻፈ አይደለም።


ሕግ የተቀረጸው በድንጋይ ጽላት በፊደል ነበር፤ ሕግ በተሰጠበትም ጊዜ የነበረው ብርሃን እየተወገደ የሚሄድ ቢሆንም እስራኤላውያን የሙሴን ፊት ትኲር ብለው ሊመለከቱት አልቻሉም፤ እንግዲህ ሞትን ያመጣ ሕግ በእንዲህ ዐይነት ክብር ከተገለጠ


ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “ቀድሞ የተሰበሩትን የድንጋይ ጽላቶች አስመስለህ በምትካቸው ሁለት ጽላቶች ቅረጽ፤ ለእነርሱ ማኖሪያ የሚሆን ታቦትም ከእንጨት ሥራ፤ እኔም ወዳለሁበት ተራራ ውጣ፤


“ስለዚህም ቃል ኪዳኑ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች በሁለት እጆቼ እንደ ያዝኩ ከተራራው ተመልሼ ወረድኩ፤ በዚያን ጊዜ የእሳት ነበልባል ከተራራው ይታይ ነበር፤


“እነሆ፥ ከዚህ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ሕዝብ ጋር የምገባው ቃል ኪዳን የሚከተለው ነው ይላል ጌታ፤ እኔ ሕጌን በአእምሮአቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።


跟着我们:

广告


广告