Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 31:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ሥራችሁን ሁሉ የምታከናውኑባቸው ስድስት የሥራ ቀኖች አሉላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእኔ ተለይቶ የተቀደሰ የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚህ ቀን ሥራ የሚሠራበት ሁሉ በሞት ይቀጣ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ በሰንበት ቀን ማንም ቢሠራ በሞት መቀጣት አለበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፥ ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ በሰንበት ቀን የሚሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ስድ​ስት ቀን ሥራ​ህን ሥራ፤ ሰባ​ተ​ኛዋ ቀን ግን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደ​ስች የዕ​ረ​ፍት ሰን​በት ናት፤ በሰ​ን​በት ቀን የሚ​ሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገ​ደል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ስድስት ቀን ሥራን ሥራ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ለእግዚአብሔር የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ በሰንበት ቀን የሚሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል።

参见章节 复制




ዘፀአት 31:15
21 交叉引用  

እግዚአብሔር ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሰባተኛው ቀን ዐረፈ።


እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “የነገው ዕለት ለእርሱ ተለይቶ የተቀደሰ የዕረፍት ቀን እንዲሆን እግዚአብሔር አዞአል፤ ስለዚህ ዛሬውኑ የምትጋግሩትን ጋግሩ፤ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፤ የተረፈው ተከፍሎ ለነገ ይቀመጥ።”


ስለዚህ ስድስት ቀን በተከታታይ ይህን ምግብ ሰብስቡ፤ የዕረፍት ቀን በሆነው በሰባተኛው ቀን ግን ምንም ምግብ አይኖርም።”


“በሳምንት ስድስት ቀን ሥራህን ሁሉ ሥራ፤ በሰባተኛው ቀን ግን ምንም ሥራ አትሥራበት፤ በዚህ ዐይነት አገልጋዮችህና ለአንተ የሚሠሩ መጻተኞች፥ እንዲሁም በሬህና አህያህ ዕረፍት አድርገው ይዋሉ።


የተቀደሰ ስለ ሆነ ሰንበትን የዕረፍት ቀን አድርጋችሁ ጠብቁት፤ ይህን የሰንበት ቀን የማይጠብቅና የሥራ ቀን አድርጎ የሚጠቀምበት ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ።


የእስራኤል ሕዝብ ለሚመጣው ትውልድ ሁሉ ይህ ቀን ጸንቶ የሚኖር የቃል ኪዳን ምልክት አድርገው ይጠብቁት፤


እኔ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ ከፈጠርኩ በኋላ ሰባተኛው ቀን ሥራዬን አቁሜ ያረፍኩበት ስለ ሆነ በእኔና በእስራኤል ሕዝብ መካከል ለዘለዓለም ጸንቶ የሚኖር ምልክት ይሁን።”


“ሥራችሁን ሁሉ የምታከናውኑባቸው ስድስት ቀኖች አሉላችሁ፤ በእርሻም ሆነ በመከር ወራት በሰባተኛው ቀን ምንም ሥራ አትሥሩ።


ሥራችሁን ሁሉ የምትሠሩባቸው ስድስት ቀኖች አሉላችሁ፤ ሰባተኛው ቀን ግን ዕረፍት ታደርጉበት ዘንድ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕለት ነው፤ በዚህ ቀን ሥራ የሚሠራበት ማንኛውም ሰው በሞት ይቀጣል፤


ስለዚህ በሰንበት ቀን በቤታችሁ እሳት እንኳ አታንድዱ።”


ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ወደ ውስጠኛው አደባባይ የሚያስገባው ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ የሚያመለክተው በር በስድስቱ የሥራ ቀኖች ዝግ መሆን አለበት፤ ነገር ግን በሰንበት ቀንና በየወሩ መባቻ ቀን ይከፈታል።


“ከዚህ የሚከተሉትን መመሪያዎች በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ቋሚ ሥርዓት አድርጋችሁ ትጠብቁአቸዋላችሁ፦ ሰባተኛው ወር በገባ በዐሥረኛው ቀን እስራኤላውያንና በእነርሱ መካከል የሚኖሩ መጻተኞች ራሳቸውን ማዋረድ አለባቸው፤ በዚያን ቀን ምንም ሥራ አይሥሩበት።


ሥራ የምትሠሩባቸው ስድስት ቀኖች አሉላችሁ፤ ሰባተኛው ዕለተ ሰንበት ግን የዕረፍት ቀን ነው፤ በዚያን ቀን ለአምልኮ ተሰብሰቡ እንጂ ምንም ሥራ አትሥሩበት፤ በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ሰንበት ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ዕለት ነው፤


ወሩ ከገባ ከዘጠነኛው ቀን የፀሐይ መጥለቂያ ሰዓት ጀምሮ እስከ ዐሥረኛው ቀን የፀሐይ መጥለቂያ ጊዜ ድረስ ለንስሓ ራሳችሁን አዋርዱ፤ ይህን ዕለት ልዩ የዕረፍት ቀን አድርጋችሁ ጠብቁት።”


ኢየሱስ በሰንበት ቀን ስለ ፈወሰ የምኲራቡ አለቃ ተቈጣና ለሕዝቡ፦ “በሳምንት ውስጥ ሥራ የሚሠራባቸው ስድስት ቀኖች አሉ፤ በእነዚህ ቀኖች እየመጣችሁ ተፈወሱ፤ በሰንበት ቀን ግን አይሆንም” ብሎ ተናገረ።


ወደ ቤታቸውም ተመልሰው ለአስከሬን የሚሆኑ ጥሩ መዓዛ ያለው ቅመምና ሽቶ አዘጋጁ፤ በሕግ መሠረት በሰንበት ቀን ዐርፈው ዋሉ።


“ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዝኩህ የሰንበትን ቀን ጠብቅ፤ ቀድሰውም፤


እንግዲህ ለእግዚአብሔር ሕዝብ የሰንበትን ዕረፍት የመሰለ ዕረፍት ገና ይቀረዋል፤


跟着我们:

广告


广告