Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 30:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በየምሽቱም መብራቶቹን ሲያበራ እንዲሁ ያድርግ፤ ይህ የዕጣን መባ አቀራረብ በሚመጡት ዘመናት ሁሉ ባለማቋረጥ የሚቀጥል መሆን አለበት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ምሽት ላይ መብራቶቹን በሚያበራበትም ጊዜ ዕጣኑን ማጠን አለበት፤ ይኸውም በሚመጡት ትውልዶች ሁሉ ዕጣኑ በእግዚአብሔር ፊት ዘወትር እንዲጤስ ነው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 አሮን በማታ ጊዜ መብራቶቹን ሲያበራ ይጠነው፥ ይህንም በትውልዳችሁ ሁሉ በጌታ ፊት ዘወትር የሚቀርብ ዕጣን ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ይህም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ወ​ትር ዕጣን ይሆን ዘንድ አሮን በማታ ጊዜ መብ​ራ​ቶ​ቹን ሲያ​በራ ያጥ​ነ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ይህን በእግዚአብሔር ፊት ለልጅ ልጃችሁ የዘውትር ዕጣን ይሆን ዘንድ አሮን በማታ ጊዜ መብራቶቹን ሲያበራ ያጥነዋል።

参见章节 复制




ዘፀአት 30:8
12 交叉引用  

እንዲህም አሉት፦ “ዖዝያ ሆይ! አንተ ለእግዚአብሔር ዕጣን ታጥን ዘንድ አይገባህም፤ ይህን ለማድረግ የተመደቡት ለእግዚአብሔር የተለዩት የአሮን ልጆች የሆኑት ካህናት ብቻ ናቸው፤ ስለዚህ ከዚህ ከተቀደሰው ስፍራ ውጣ፥ እግዚአብሔር አምላክን አሳዝነሃል፤ ይህም ከእግዚአብሔር ዘንድ ክብርን የሚያስገኝልህ ድርጊት አይደለም።”


ጸሎቴን እንደ ዕጣን፥ የተዘረጉትን እጆቼን እንደ ማታ መሥዋዕት አድርገህ ተቀበል።


እነዚህንም እስከ ዐሥራ አራተኛው ቀን ጠብቁአቸው። በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ የእስራኤል ኅብረተሰብ ሁሉ እንስሶቹን ይረዱ።


ለመቅረዙም ሰባት መብራቶች ሠርተህ ከፊት ለፊት በኩል እንዲያበሩ፥ ከፍ አድርገህ አስቀምጣቸው።


አሮንና ልጆቹ ከምሽት እስከ ንጋት ይበራ ዘንድ የእግዚአብሔር መገኛ ከሆነው ፊት ከቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ካለው መጋረጃ ውጪ ያኑሩት፤ ይህም በእስራኤል ሕዝብና ወደፊትም በሚነሣው ትውልድ ዘንድ ቋሚ ሥርዓት ሆኖ ይኑር።


አሮን በየማለዳው መብራቶችን ለማዘጋጀት በሚመጣበት ጊዜ መልካም መዓዛ ያለውን ዕጣን በመሠዊያው ላይ ይጠን።


በዚህ መሠዊያ ላይ ማናቸውም የተከለከለ ዕጣን፥ የእንስሳ መሥዋዕት፥ ወይም የእህል ቊርባን አታቅርብ፤ የወይን ጠጅ መባም አታፍስስበት።


ማነው የሚፈርድ? ኢየሱስ ክርስቶስ ይፈርድባቸዋልን? እርሱ ስለ እኛ የሞተ፥ ከሞት ተነሥቶ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ የተቀመጠ፥ ስለ እኛም የሚማልድ ነው።


ባለማቋረጥ ጸልዩ፤


ስለዚህ እነርሱን ለማማለድ ለዘለዓለም ሕያው ሆኖ ስለሚኖር በእርሱ አማካይነት ወደ እግዚአብሔር የሚመጡትን ሁሉ በፍጹም ሊያድናቸው ይችላል።


ክርስቶስ የእውነተኛይቱ “መቅደስ” ምሳሌ ወደ ሆነችውና በሰው እጅ ወደተሠራችው ቅድስተ ቅዱሳን አልገባም፤ እርሱ አሁን ስለ እኛ በእግዚአብሔር ፊት ለመታየት ወደ ሰማይ ገባ።


እርሱንም ከእስራኤል ነገድ ሁሉ ወደ መሠዊያዬ እንዲወጣ፥ እጣን እንዲያጥን፥ በፊቴ ኤፉድ እንዲለብስ፥ የእኔ ካህን ይሆን ዘንድ መረጥሁት፤ ለቀድሞ አባትህ ልጆችም የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡትን የሚቃጠል መሥዋዕት ሰጠኋቸው።


跟着我们:

广告


广告