Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 30:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ሠርተህ መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉት መሎጊያዎች እንዲገቡበት ከክፈፉ ሥር አያይዛቸው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 መሠዊያውን ለመሸከም የሚያገለግሉትን መሎጊያዎች የሚይዙ፣ ከክፈፉ በታች ትይዩ የሆኑ ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን ለመሠዊያው አብጅ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከአክሊሉ በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን አድርግለት፤ በዚህና በዚያ በሁለቱ ጎን ታደርጋቸዋለህ፤ በእነርሱ እንዲሸከሙም የመሎጊያዎቹ ማስገቢያ ይሁኑ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ከክ​ፈ​ፉም በታች ሁለት የወ​ርቅ ቀለ​በ​ቶች አድ​ር​ግ​ለት። በዚ​ህና በዚያ በሁ​ለቱ ጐን ታደ​ር​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱን ያነ​ሡ​ባ​ቸው ዘንድ የመ​ሎ​ጊ​ያ​ዎቹ መግ​ቢያ ይሁኑ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከክፈፉም በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶች አድርግለት። በዚህና በዚያ በሁለቱ ጎን ታደርጋቸዋለህ፤ ለመሸከምም የመሎጊያዎች ስፍራ ይሁኑ።

参见章节 复制




ዘፀአት 30:4
8 交叉引用  

አራት የወርቅ ዋልታዎችንም ሠርተህ ሁለቱን በአንድ በኩል፥ ሁለቱንም በሌላ በኩል በማድረግ ከአራቱም እግሮቹ ጋር እንዲያጣብቁ አድርግ፤


እነዚህንም መሎጊያዎች በታቦቱ አራት ማእዘን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባ።


ጠረጴዛውንም ለመሸከም መሎጊያዎቹ የሚሰኩባቸው ቀለበቶች ከክፈፉ ጋር የተቀራረቡ ይሁኑ።


ተራዳዎችንም በወርቅ ለብጣቸው፤ ለመወርወሪያዎቹም መያዣ እንዲሆኑ የወርቅ ዋልታዎች አብጅላቸው፤ መወርወሪያዎቹም በወርቅ የተለበጡ ይሁኑ፤


እንደ መረብ ሆኖ የተሠራ የነሐስ መከላከያ አብጅለት፤ ለመከላከያውም አራት የነሐስ ቀለበቶች በአራቱም ማእዘን አድርግለት።


መሠዊያውን መሸከም በሚያስፈልግበትም ጊዜ መሎጊያዎቹን ከመሠዊያው በእያንዳንዱ ጐን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አግባ።


የመሠዊያውን ጫፍ፥ አራት ጐኖቹንና ጒጦቹን ሁሉ በንጹሕ ወርቅ ለብጠው፤ የወርቅ ክፈፍም አብጅለት።


መሎጊያዎችንም ከግራር እንጨት ሠርተህ በወርቅ ለብጣቸው።


跟着我们:

广告


广告