Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 30:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

35 እንደ ሽቶ የተቀላቀለ ዕጣን አድርገህ ተጠቀምባቸው። ንጹሕና ቅዱስ ይሆንም ዘንድ ጨው ጨምርበት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

35 በቀማሚ እንደ ተሠራ ጣፋጭ መዐዛ ያለው የተቀመመ ዕጣን አብጅ፤ በጨው የተቀመመ፣ ንጹሕና የተቀደሰ ይሁን።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

35 ቀማሚ እንደሚቀምመው፥ በጨው የተቀመመ፥ ንጹሕና ቅዱስ አድርገህ ዕጣን አዘጋጅ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

35 በቀ​ማሚ ብል​ሃት እንደ ተሠራ፥ የተ​ቀ​መመ ንጹ​ሕና ቅዱስ ዕጣን አድ​ር​ገው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

35 በቀማሚ ብልሃት እንደ ተሠራ፥ በጨው የተቀመመ ንጹሕና ቅዱስ ዕጣን አድርገው።

参见章节 复制




ዘፀአት 30:35
13 交叉引用  

ካህኑ ሳዶቅም ከተቀደሰው ድንኳን ይዞት የመጣውን የቅባት ዘይት መያዣ ቀንድ ወስዶ ሰሎሞንን ቀባው፤ በዚህን ጊዜ እምቢልታ ነፉ፤ ሕዝቡም ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው “ረጅም ዕድሜ ለንጉሥ ሰሎሞን!” አሉ፤


ከካህናቱም ወገኖች አንዳንዶቹ ቅመማቅመሙን የማዋሐዱን ኀላፊነት ወሰዱ።


በአሮን ራስና ጢም ላይ እንደሚፈስስ፥ እስከ ልብሱም ዘርፍ ድረስ እንደሚዘልቅ፥ መልካም መዓዛ እንዳለው የወይራ ዘይት ነው።


እንግዲህ እነዚህን ልብሶች ለወንድምህ ለአሮንና ለልጆቹ አልብሳቸው፤ በክህነት ያገለግሉኝም ዘንድ የወይራ ዘይት በመቀባት የክህነትን ማዕርግ ትሰጣቸዋለህ፤ ትቀድሳቸዋለህም፤


እንደ ሽቶ ቀላቅለህ የተቀደሰ የቅባት ዘይት ሥራ፤


እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የእያንዳንዳቸው ሚዛን እኩል የሆነ ጣፋጭ ቅመሞችን ይኸውም የሚንጠባጠብ ፈሳሽነት ያለው ሙጫ፥ በዛጎል ውስጥ የሚገኝ ሽቱ፥ የሚሸት ሙጫና ጣፋጭ ሽታ ያለው ዕጣን ወስደህ፥


ከእርሱም ጥቂቱን ወስደህ በመውቀጥ ካላምከው በኋላ ወደ ድንኳኑ ወስደህ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት እርጨው፤ ይህንንም ዕጣን ፍጹም የተቀደሰ እንዲሆን አድርግ።


ሽቶና መልካም መዓዛ ያለው ቅባት ሰውን ደስ እንደሚያሰኝ የወዳጅ ምክርም እንዲሁ ደስ ያሰኛል።


የምትቀባው ሽቱ መልካም መዓዛ አለው፤ ስምህን መጥራት ሽቱን እንደ መርጨት ነው፤ ቈነጃጅትም የሚያፈቅሩህ ስለዚህ ነው።


እንደ ነጋዴ ቅመም መልካም መዓዛ ያላት፥ በዕጣንና በከርቤ መዓዛ እየተወገደ እንደ ጢስ ዐምድ ሆና ያቺ ከበረሓ የምትመጣው ማን ናት?


ከመሠዊያው የሚቃጠል የእሳት ፍም በጥናው ሞልቶም ሁለት እፍኝ ጣፋጭ ሽታ ያለውን የተወቀጠ ደቃቅ ዕጣን በመውሰድ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ያግባ፤


ይህ የእህል ቊርባን ስለ ሆነ በእህል ቊርባንህ ሁሉ ላይ ጨው ጨምርበት፤ የአምላክህን የጨው ቃል ኪዳን አትተው፤ በቊርባኖች ሁሉ ጨው መግባት አለበት።


በዚያን ጊዜ ማርያም ዋጋው እጅግ የከበረ ከንጹሕ ናርዶስ የተሠራ፥ ግማሽ ሊትር የሚሆን አንድ ብልቃጥ ሽቶ ወስዳ፥ የኢየሱስን እግሮች ቀባች፤ በጠጒርዋም አበሰቻቸው፤ ቤቱም በሽቶው መዓዛ ተሞላ።


跟着我们:

广告


广告