Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 29:42 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

42 ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ይህ የሚቃጠል መሥዋዕት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ መቅረብ አለበት፤ እኔ ሕዝቤን የምገናኘውና አንተንም የማነጋግርበት ስፍራ ይኸው ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

42 “ይህ የሚቃጠል መሥዋዕት በእግዚአብሔር ፊት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ላይ በሚመጡት ትውልዶች ዘወትር ይደረጋል፤ በዚያ እገናኝሃለሁ፤ እናገርሃለሁም፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

42 ከአንተ ጋር ለመነጋገር በዚያ በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን መግቢያ፥ ይህ ዘወትር በትውልዶቻችሁ በጌታ ፊት የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

42 በዚያ እና​ገ​ርህ ዘንድ ለአ​ንተ በም​ገ​ለ​ጥ​በት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ወ​ትር መሥ​ዋ​ዕት ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

42 ለአንተ እናገር ዘንድ ከእናንተ ጋር በምገናኝበት በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ፥ በእግዚአብሔር ፊት ይህ ዘወትር ለልጅ ልጃችሁ የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል።

参见章节 复制




ዘፀአት 29:42
10 交叉引用  

እኔም በዚያ ለአንተ እገለጥልሃለሁ፤ በመክደኛው ላይ በተሠሩት ክንፍ ባላቸው በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ሆኜ ለእስራኤል ሕዝብ የምታቀርበውን ትእዛዞቼን ሁሉ እሰጥሃለሁ።


አሮንና ልጆቹ ከምሽት እስከ ንጋት ይበራ ዘንድ የእግዚአብሔር መገኛ ከሆነው ፊት ከቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት ለፊት ካለው መጋረጃ ውጪ ያኑሩት፤ ይህም በእስራኤል ሕዝብና ወደፊትም በሚነሣው ትውልድ ዘንድ ቋሚ ሥርዓት ሆኖ ይኑር።


ሁለተኛውንም ጠቦት በምሽት ጊዜ መሥዋዕት አድርገህ አቅርብ፤ በማለዳው መሥዋዕት ባቀረብከውም መጠን ተመሳሳይ ዱቄት፥ ዘይትና ወይን ጠጅ አቅርብ፤ ይህ ለእኔ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የምግብ መባ ነው፤ መዓዛውም እኔን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።


በዚህም ከሕዝቤ ከእስራኤል ጋር እገናኛለሁ፤ ክብሬም ይህን ስፍራ የተቀደሰ ያደርገዋል።


ከእርሱም ጥቂቱን ወስደህ በመውቀጥ ካላምከው በኋላ ወደ ድንኳኑ ወስደህ በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት እርጨው፤ ይህንንም ዕጣን ፍጹም የተቀደሰ እንዲሆን አድርግ።


የእስራኤል ሕዝብ በሰፈሩበት ቦታ ሁሉ ሙሴ ድንኳኑን ከሰፈሩ ራቅ ባለ ቦታ ይተክለው ነበር፤ እርሱም “ድንኳን” ተብሎ ተጠራ፤ እግዚአብሔርን መጠየቅ የሚፈልግ ሁሉ ወደዚያ ይሄድ ነበር።


በዚያም ያ ሰው በአጠገቤ ቆሞ ነበር፤ እግዚአብሔርም ከቤተ መቅደሱ እንዲህ እያለ ሲናገረኝ ሰማሁ፤


በዚህም ዓይነት የበጉ ጠቦት፥ የእህሉ ቊርባንና ዘይቱ በየማለዳው መቅረብ ያለበት የሚቃጠል መሥዋዕት ነው።”


እነርሱንም ወደ መገናኛው ድንኳን ወስደህ አንተን በማነጋግርበት ስፍራ በታቦቱ ፊት ለፊት አኑራቸው፤


ከመጀመሪያው ጠቦት ጋር የመጠጥ መባ ሆኖ እንዲቀርብ አንድ ሊትር ጠንካራ መጠጥ በመሠዊያው ላይ አፍስሱበት።


跟着我们:

广告


广告