Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 29:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “ኰርማውን ወደ ድንኳኑ ፊት ለፊት አምጥተህ፥ አሮንና ልጆቹ እጃቸውን በራሱ ላይ እንዲጭኑበት አድርግ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “ወይፈኑን በመገናኛው ድንኳን ፊት ለፊት በማምጣት አሮንና ወንዶች ልጆቹ በራሱ ላይ እጆቻቸውን ይጫኑበት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ወይፈኑን ወደ መገናኛው ድንኳን በር ፊት ታቀርበዋለህ፤ አሮንና ልጆቹም እጆቻቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭናሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “ወይ​ፈ​ኑ​ንም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን በር ታቀ​ር​በ​ዋ​ለህ፤ አሮ​ንና ልጆ​ቹም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን በር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት እጆ​ቻ​ቸ​ውን በወ​ይ​ፈኑ ራስ ላይ ይጭ​ናሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ወይፈኑንም ወደ መገናኛው ድንኳን በር ፊት ታቀርበዋለህ፤ አሮንና ልጆቹም እጆቻቸውን በወይፈኑ ራስ ላይ ይጭናሉ።

参见章节 复制




ዘፀአት 29:10
13 交叉引用  

ኰርማውን በድንኳኑ ደጃፍ በእኔ በእግዚአብሔር ፊት ዕረደው።


“ከሁለቱ የበግ አውራዎች አንዱን ወስደህ አሮንና ልጆቹ እጃቸውን በራሱ ላይ እንዲጭኑ አድርግ።


“ለክህነት ሥርዓት የተመደበውን ሌላውንም አውራ በግ ወስደህ አሮንና ልጆቹ እጃቸውን በራሱ ላይ እንዲጭኑበት ንገራቸው፤


ሁላችንም እንደ በጎች ባዝነን ነበር፤ ሁላችንም ወደ ራሳችን መንገድ ሄደን ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።


ይህንን ሁሉ ከፈጸምክ በኋላ ነውር የሌለባቸውን አንድ ወይፈንና አንድ አውራ በግ ከመንጋው ወስደህ፥


ሰውየው ለሚቃጠል መሥዋዕት ባቀረበው እንስሳ ራስ ላይ እጆቹን ይጫን፤ እርሱም ለኃጢአቱ ማስተስረያ የሰመረ መሥዋዕት ይሆንለታል።


ሁለት እጆቹን በፍየሉ ራስ ላይ ይጭናል፤ የሕዝቡን ክፋት፥ ኃጢአትና ዐመፅ ሁሉ በመናዘዝ አዛውሮ በፍየሉ ራስ ላይ ያሸክመዋል፤ ከዚህ በኋላ ለዚህ ሥራ የተመደበ ሰው ፍየሉን ነድቶ ወደ በረሓ ይወስደዋል።


መሥዋዕት አቅራቢው ሰው መባ አድርጎ በሚያቀርበው እንስሳ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ ይረደው፤ የአሮን ዘር የሆኑ ካህናትም ደሙን ተቀብለው በመሠዊያው ዙሪያ ይርጩት።


ኰርማውንም ወደ ድንኳኑ ደጃፍ አምጥቶ እጁን በእንስሳው ራስ ላይ በመጫን በእግዚአብሔር ድንኳን ፊት ይረደው።


ከዚህም በኋላ ሙሴ ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚቀርበውን ኰርማ አመጣ፤ አሮንና ልጆቹ በኰርማው ራስ ላይ እጃቸውን ጫኑ፤


ከዚያም በኋላ ሙሴ ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚቀርበውን የበግ አውራ አመጣ፤ አሮንና ልጆቹ በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ፤


ከዚህ በኋላ ሌዋውያን እጆቻቸውን በሁለቱ ኰርማዎች ላይ ይጭናሉ፤ አንዱ ስለ ኃጢአት ስርየት የሚቀርብ መሥዋዕት፥ ሌላው የሚቃጠል መሥዋዕት ይሆናል፤ ለሌዋውያን ለማስተስረይ የሚፈጸመው ሥነ ሥርዓት በዚህ ዐይነት ይከናወናል።”


እኛ በክርስቶስ የእግዚአብሔር ጽድቅ ተካፋዮች እንድንሆን እግዚአብሔር ኃጢአት የሌለበትን ክርስቶስን የእኛን ኃጢአት እንዲሸከም አደረገው።


跟着我们:

广告


广告