ዘፀአት 28:40 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም40 “ለአሮንም ልጆች ክብርና ውበት ይሆንላቸው ዘንድ ሸሚዞችን፥ መታጠቂያዎችንና ቆቦችን ሥራላቸው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም40 የአሮን ወንድ ልጆች ክብርና ማዕርግ እንዲኖራቸው ሸሚዞችን፣ መታጠቂያዎችን፣ የራስ ማሰሪያዎችን አብጅላቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)40 ለአሮን ልጆች እጀ ጠባቦችን፥ መታጠቂያዎችንና ቆቦችን ለክብርና ለጌጥ ትሠራላቸዋለህ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)40 ለአሮንም ልጆች የበፍታ ቀሚሶችን፥ መታጠቂያዎችንም፥ ቆቦችንም ለክብርና ለመለያ ታደርግላቸዋለህ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)40 ለአሮንም ልጆች ሸሚዞችን መታጠቂያዎችንም ቆቦችንም ለክብርና ለጌጥ ታደርግላቸዋለህ። 参见章节 |