ዘፀአት 26:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም31 “ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ከፈይ ከተፈተለ በፍታ መጋረጃን ሥራ፤ በእርሱም ላይ ኪሩቤል፥ በጥልፍ ጥበብ እንዲሳሉ አድርግ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም31 “ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ መጋረጃ ሥራ፤ እጀ ጥበብ ባለሙያም ኪሩቤልን ይጥለፍበት። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)31 “መጋረጃውንም ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም አድርግ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእርሱ ላይ ይሁኑ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)31 “መጋረጃውንም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊም፥ ከቀይም ግምጃ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም አድርግ፤ በሽመና ሥራም ኪሩቤልን ሥራ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)31 መጋረጃውንም ከሰማያዊ ከሐምራዊም ከቀይም ግምጃ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም አድርግ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእርሱ ላይ ይሁኑ። 参见章节 |