Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፀአት 22:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 “እናንተ ለእኔ የተለያችሁ ሰዎች ትሆኑልኛላችሁ፤ ስለዚህ አውሬ በሜዳ የገደለውን የማንኛውንም እንስሳ ሥጋ አትብሉ፤ ለውሾች ጣሉት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 “እናንተ ለእኔ ቅዱስ ሕዝብ ትሆናላችሁ፤ ስለዚህ አውሬ የዘነጠለውን የእንስሳ ሥጋ አትብሉ፤ ለውሾች ስጡት።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ቅዱስ ወገን ትሆ​ኑ​ል​ኛ​ላ​ችሁ፤ ስለ​ዚህ አውሬ የገ​ደ​ለ​ውን ሥጋ ለውሻ ጣሉት እንጂ አት​ብ​ሉት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ቅዱስ ወገን ትሆኑልኛላችሁ፤ ስለዚህ በምድረ በዳ አውሬ የቧጨረውን ሥጋ ለውሻ ጣሉት እንጂ አትብሉት።

参见章节 复制




ዘፀአት 22:31
14 交叉引用  

ለራሳቸውና ለልጆቻቸው ሚስቶች የሚሆኑ ከእነዚያ ወገኖች አግብተዋል፤ አጋብተዋልም፤ ቅዱሱን ዘር ከሌሎች ከአካባቢው አሕዛብ ጋር ቀላቅለዋል፤ በዚህ እምነተ ቢስ በሆነ ተግባር መሪዎቹና ባለ ሥልጣኖቹ ግንባር ቀደም ሆነዋል።”


እኔም እንዲህ ስል መለስኩ፦ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ይህስ ከቶ አይሁን! እኔ ከቶ ረክሼ አላውቅም፤ ከሕፃንነቴ ጀምሮ የበከተ ወይም አውሬ የገደለው ከብትን ሥጋ የበላሁበት ጊዜ የለም፤ ጸያፍ ምግብም አልበላሁም።”


ካህናቱ ሞቶ የተገኘውን ወይም ሌላ አውሬ የገደለውን የወፍ ወይም የእንስሳ ሥጋ አይብሉ።”


“ለእስራኤል ሕዝብ ይህን ንገር፦ ‘እኔ አምላካችሁ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ፤


ስለዚህም ንጹሓን በሆኑትና ንጹሓን ባልሆኑት እንስሶችና ወፎች መካከል ልዩነት አድርጉ፤ እኔ ርኩሳን ናቸው ብዬ ለይቼ ባስታወቅኋችሁና በምድር ላይ በሚገኙ እንስሶች፥ ወፎችና ሌሎችም ነገሮች ሁሉ ራሳችሁን አታርክሱ፤


ሞቶ የተገኘውን ወይም አውሬ የገደለውን የእንስሳ ሥጋ አይብላ፤ እርሱን ቢበላ ያረክሰዋል፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።


ሞቶ የተገኘ እንስሳ ወይም አውሬ የገደለው እንስሳ ስቡ ለሌላ አገልግሎት ይዋል እንጂ ማንም ሰው አይብላው።


ጴጥሮስ ግን “ጌታ ሆይ! አይሆንም! እኔ ንጹሕ ያልሆነ ወይም ርኩስ ነገር በልቼ አላውቅም” አለ።


ይልቅስ ‘ለጣዖት በመሠዋቱ ምክንያት የረከሰ ምግብን አትብሉ፤ ከዝሙት ራቁ፤ ሳይታረድና ደሙም ሳይፈስ ታንቆ የሞተ እንስሳ ሥጋን አትብሉ፤ ደምንም አትብሉ’ ብለን እንጻፍላቸው።


“ሞቶ የተገኘውን እንስሳ አትብላ፤ በመካከልህ የሚኖሩ የውጪ አገር ሰዎች እንዲመገቡት ፍቀድላቸው፤ ወይም ለውጪ አገር ሰዎች በዋጋ ልትሸጥላቸው ትችላለህ። አንተ ግን ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የተለየህ ሕዝብ ነህ። “የፍየልን ግልገል በእናቱ ወተት አትቀቅል።


跟着我们:

广告


广告