ዘፀአት 19:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 በሦስተኛው ቀን ማለዳ የነጐድጓድ ድምፅ አስተጋባ፤ የመብረቅ ብልጭልጭታና ጥቅጥቅ ያለ ደመና በተራራው ላይ ታየ፤ እንዲሁም ከፍተኛ የሆነ የእምቢልታ ድምፅ ተሰማ። ሰዎቹም በሰፈሩበት ቦታ ፈርተው ተንቀጠቀጡ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 በሦስተኛውም ቀን ጧት ከባድ ደመና በተራራው ላይ ሆኖ ነጐድጓድና መብረቅ እንዲሁም ታላቅ የቀንደ መለከት ድምፅ ነበር፤ በሰፈሩ ያሉት ሁሉ ተንቀጠቀጡ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 እንዲህም ሆነ በሦስተኛው ቀን ማለዳ ነጎድጓድ፥ መብረቅና ከባድ ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩ የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን በማለዳ ጊዜ ነጐድጓድና መብረቅ፥ ከባድም ደመና፥ ጉምም በሲና ተራራ ላይ ሆነ፤ እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምፅ ተሰማ፤ በሰፈሩም የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 እንዲህም ሆነ፤ በሦስተኛው ቀን በማለዳ ጊዜ ነጎድጓድና መብረቅ ከባድም ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩም የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ። 参见章节 |